የመብት ተሟጋቹ ድርጅት፣ «ሂውመን ራይትስ ዎች» የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞጌሪኒን የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ጉብኝትን ተከተሎ አንድ የወቀሳ ደብዳቤ ጽፏል።
ድርጅቱ በደብዳቤዉ የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ሞጌሪኒ ከጉብኝታቸው በኋላ ባወጡት በመግለጫቸዉ በኢትዮጵያ ስለሚታየዉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አልጠቀሱም በማለት ወቅሷል። ይህ ይፋዊ መግለጫቸዉ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ስላካሄዱት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከመዘርዘር ዉጭ፤ ስለአስቸኳዩ ጊዜ አዋጁም ሆነ በእስር ላይ ስለሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ጋዜጠኞች ጉዳይ እንዳላነሱም «ሂውመን ራይትስ ዎች» ዘርዝሯል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ