የአዉሮጳ ኅብረት ና ስደተኞች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.02.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የአዉሮጳ ኅብረት ና ስደተኞች

የወቅቱ የአዉሮጳ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኔዘርላንድ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ አምስተርዳም ከተማ የኅብረቱ ሀገሮች የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ጋብዛ ኅብረቱን እየፈተነዉ በሚገኘዉ የስደተኞች ጉዳይና በኅብረቱና በኢራን መካከል ስለሚኖረዉ አዲስ ግንኙነት አወያያታለች።


በዉይይቱ የቱርክና የባልካን ሀገሮች የዉጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የተሳተፉ ሲሆን የዉይይቱ ዓላማ የስደተኞች ችግር የሁሉም ችግር መሆኑን የበለጠ በመገንዘብ የኅብረቱ አባል ሀገሮችም ሆኑ አዋሳኝ እጩ አባል ሃገሮች ተባብረዉና በቅንጅት በመሥራት ሁሉም ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ የጋራ መግባባት ለመፍጠር መሆኑ ተነግሮአል። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ልኮልናል


ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic