የአሸባብ ዉስጣዊ ችግር | አፍሪቃ | DW | 09.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የአሸባብ ዉስጣዊ ችግር

የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ የሆነና የሶማሊያዉ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አልሸባብን ከሰባት ዓመት በፊት የተቀላቀለ ግለሰብ በጎርጎሮሳውያኑ ህዳር ስድስት ራሱን ለሶማሊያ መንግስት አሳልፎ ሰጥቷል። ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ በ17 ዓመቱ አሸባብን የተቀላቀለ ስሆን በድረገፆች የፅንፈኞችን አሳማኝ ንግግሮች የሚለጥፍና የ«አይ ኤስ» ቡድን ቀንደኛ ደጋፊ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:41

የአልሸባብ ዉስጣዊ ጠብ

የሽብር ጉዳይ አዋቂዎች ፣ ትውልደ ሶማሊያዊ፣ እጁን መስጠት ያሰበበት ምክንያት አልሸባብ በክፍለ ጦሩ ሙስጥ የ«አይ ኤስ» ደጋፊ የሆኑትን ማጥቃት ስለጀመረ ነዉ ይላሉ። ማክሰኞ ሌላ የሳን ድኤጎ ነዋሬ ከአሸባብ አፈንግጦ እጁን ሰጥቷል። የሁለቱን ትውልደ ሶማሊያዊ አሜሪካውያን ከአሸባብ የማፈንገች ጉዳይ እና በአልሸባብ ዉስጥ የተፈጠረዉን መካፋፈል አስመልክቶ ዶቼቬለ በለንደን ዩኒቨርስቲ የኦሪዬንታል እና የአፍርካ ጥናት ትምርት ክፍል የልማት ጥናት መምህር የሆኑትን ላኡራ ሃሞንድ ስናገሩ፣ "እኔ እንደማስበዉ አዲስ ባይሆንም የሆነ ጠብ እንዳለ ነዉ። በአንድ ጎራ ራሳቸዉን ወደ አልቃይዳ ማቆራኘት የሚፈልጉ፣ በሰፊዉ፣ የሽግግር መረብ ያላቸዉ እና በሌላኛዉ ጎራ ደግሞ የሶማሊያው ዉጊያ ላይ ብቻ ማነጣጠር የሚፈልጉ እና ብዙም ስለ አለማቀፋዊ ጂሃድ ያማያስባቸዉ መሃል ጠብ አለ። እሱ አንድ ሆኖ እያለ፣ ሌላኛዉ ደግሞ በአሁኑ ግዜ ከአልቃይዳ ጋር የጋራ ግንባር መፍጠር የሚፈልጉና እና በአብዛኛዉ ደግሞ ከየ«አይ ኤስ» ጋር መተባበር የሚፈልጉ መሃል ጠብ አለ።"

ላኡራ ሃሞንድ አሸባብ የደከመ ባይመስላቸዉም ይህ አይነቱ ዉጥረትና መከፋፈል ረዥም ግዜ አሰቆጥረዋል ይላሉ። ይህም በአልሸባብ ላይ ትልቅ ጉዳት አይኖረውም ። ሆኖም በሶማሊያ ዉስጥ ከባድ የደህንነት ስጋት ማስከተል ችሏል። ይሁን እንጅ በአሸባብ መሪዎች መሃል ያለዉ ዉጥረት የአሸባብን ስኬታማነት ገድቧል ይላሉ የልማት ጥናት መምህር የሆኑት ላኡራ ሃሞንድ። አሸባብ በጣም የተከፋፈለ ባህር አለዉ እናም መሬት ላይ የሚያደረጋቸዉ እንቅስቃሴዎች እና ከእንቅስቃሴዎቹ ጋር አባላቶቹ የተጣመሩበት መንገድ ከእንቅስቃሴያቸዉ ዉስጥ ከየትኛዉ መሪ ጋር ራሳቸዉን በጣም እንዳቆራኙት ይወስናልም ይላሉ ላኡራ ሃሞንድ።


ቦኮ ሃራም አሁን ከ«አይ ኤስ» ጋር መቆራኘቱ የሚታወቅ ነዉ፣ ይህ ማለት አሸባብም ቢሰነጣጠቅ አንድ ቀን ተነስቶ ከ«አይ ኤስ» ወይም ከአልቃይዳ ጋር ተቆራኝቻለዉ ማለት ይችል ይሆን ሲል ዶቼ ቬሌ ላቀረበላቸዉ ጥያቄ ሃሞንድ ስመልሱ፣ "አሸባብ ዉስጥ ያሉ ራሳቸዉን ከIS ጋር ማቆራኘት የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ ። ከቅርብ ወራት ወዲህ ደግሞ «አይ ኤስ» ከአልቃኤዳ በላይ የብዙዎቹን ቀልብ መሳብ ችሎዋል ። እናም ገንዘብ በመሰብሰብና ታዋጊዎችን በመቅጠር ስኬታማ የሆነ ይመስላል። ዲያስፖራ ሶማሊያዊያኖች ቢሆኑም አብዛኛዎቹ በIS ተስቦዋል። የአልሸባብ አባሎችም የሱ አካል የመሆን ፍላጎት አለቸዉ። በሌላ በኩል፣ ብዙዎቹ ከአልቃኤዳ ጋር ረዥም ግኑኝነት ያላቸዉና በፈጠሩት ግኑኝነት የቀጠሉና ደስተኞች ናቸዉ።"


በቅርቡ በሴሜናዊ ኬንያ ብዙ ሰዎች በአንድ ላይ የተቀበሩበት መቃብር መገኘቱ ይታወሳል ። የተገደሉት ሶማሌዎች መሆናቸዉም ይነገራል። የኬንያ መንግስት ግን ይህን አስተባብሏል። ይህ ማለትም አልሻባብ ኬንያ ዉስጥ ያሉ ሶማሌዎችን ለመቅጠር እድል እንደሚሰጠዉ የልማት ጥናት መምህር የሆነችዉን ላኡራ ሃሞንድ ለዶቼ ቬሌ ተናግሮዋል።

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic