በቅርቡ በ «አዲስ ጥበብና ባህል ተቋም »ተሰርቶ የወጣው የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰን የመጨረሻ ህይወት የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም እያወዛገበ ነው ።
የአርቲስቱ ልጆች ፊልሙ በህገ ወጥ መንገድ ታትሞ ለግል ጥቅም እየዋለ ነው ሲሉ ፣ የአዲስ ጥበብና ባህል ተቋም ደግሞ ከአርቲስቱ ባለቤት ሙሉ ህጋዊ ፈቃድ እንደተሰጠውና የቅጂ ባለቤትነት መብት እንዳለውም ይናገራል ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ