የአምቦ ግጭት እና የነዋሪዎች ስጋት | ኢትዮጵያ | DW | 26.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአምቦ ግጭት እና የነዋሪዎች ስጋት

በኦሮሚያ ክልል አምቦ ዉስጥ መንግሥት የሚቃወሙ ወጣቶች እና ፀጥታ አስከባሪዎች ተጋጭተዉ በትንሽ ግምት 8 ሰዎች ሲገደሉ፤ ሌሎች ከ15 መቁሰላቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:34

ግጭት በአምቦ

ከአዲስ አበባ በ360 ክሎሜትር ገደማ ላይ ከሚገኘዉ ከፍንጫ ስኳር ፋብርካ ሶስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ስኳር ጭነው በአምቦ ከተማ በማለፍ ሳሉ ራሳቸውን «ቄሮዎች» ብለው በሚጠሩ ወጣቶች ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለመረዳት ተችለዋል። አንድ ከባድ ተሽከርካሪም በአምቦና በጉደር ከተማ መካካል ቆሞ እንደሚገኝም ያነጋገርናቸዉ ሰዎች ጠቁሟል።

ለቁጥጥሩም መነሻ የሆነዉ ከባድ ተሽከርካሪዎቹ «ሕገ ወጥ ስኳር» ጭነዋል፣ «ስኳሩን ጭነዉ ጉዦ የጀመሩበትና አምቦ ከተማ የደረሱበት ቀንም እጅግ ሰፊ ልዩነት አለዉ» እንዲሁም «የስኳር እጥረት በከተማዉ ስላለ ማሕበረሰቡ እንዲጠቀም» የሚሉ ሚክንያቶች ተነሰተዋል። ርምጃዉ ወደ ተቃዉሞ እንዳመራና ሌሎችም ችግሮች እንደፈጠረ የአምቦ ከተማ የኮሙኒኬሼን ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ።

ተሽከርካርዎቹ የያዙት የጭነት ፍቃድ ወረቀት ጊዜዉ ያለፈበት እንደሆነ ያረጋገጡት አቶ ጋዲሳ አሸከርካርዎቹ «ለደንነታቸዉ ሲባል ፖሊስ ጣብያ» እንደሚገኙ ተናግረዋልም። ትላንት ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥዋት ወጣቶቹ ስኳሩን እየጠበቁ እንደነበረ ኃላፊዉ ጠቁመዋል።

የፀጥታ አካሉ በወሰዱት ርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸዉንና ከ15 በላይ ሰዎች መቁሰላቸዉን በወሬ ደረጃ እንዳለ አቶ ጋዲሳ ይናገራሉ። ይሁን እንጅ ከሳዓታት በፊት አምቦ ሆስፕታል በመገኘት ስምንት ሰዎች የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ሲሉ ዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

በዶይቼ ቬሌ የዋትስአፕ ገፅ ላይ ስማቸዉን ያልጠቅሱ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ «በአሁኑ ሰዓት አጋዚዎች ወንዶች ዶርም ገብተው እየደበደቡ ነው» ስሉ አስተያየታቸዉን ልከውልናል። ቱክስ ሲሰማ ስለነበረ የሟቾች ቁጥርም ከዛ በላይ ይሆናል የሚል ግምት እንደነበረው ተማሪዉ ይናገራል።

የፀጥታ ሁኔታዉ አስቸጋሪ መሆኑንም አቶ ጋድሳ ተናግረዉ ከተማዋ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደምትገኝም ተናግረዋል።

የክልሉ የኮሙኒኬሼን ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ጥዋት ሰዎች እንደቆሰሉና ሕይወት እንዳለፈም በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ አስፍረዋል።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ በከተማዉ ያለዉ ሁኔታ አስከፊ መሆኑን ገልጸው የተጎዱትን ሰዎች ፎቶግራፍ ዛሬ ከሰዓት በፌስቡክ ገፃቸዉ ላይ አጋርተዋል።

ያነጋገርናቸዉ ሰዎች እንደሚሉት አስከሬናቸዉ ሆስፒታል ያልደረሰ ሰዎች ሊኖሩ ሥለሚችሉ የሟቾቹ ቁጥር መጨመሩ አይቀርም።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic