የአሜሪካ እና የእስራኤል ውዝግብ  | ዓለም | DW | 30.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአሜሪካ እና የእስራኤል ውዝግብ 

«የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው » የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:43

አሜሪካን እና እሥራኤል

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እስራኤል ምሥራቅ እየሩሳሌም እና በዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ  የምታካሂደው የሰፈራ ግንባታ ህገ ወጥ ነው ሲል ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ካሳለፈ ወዲህ እሥራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ እየተወዛገቡ ነው ።  ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅ ን በድምጽ የመሻር መብትዋን ተጠቅማ ውሳኔው እንዳያልፍ አለማድረጓ እስራኤልን አስቆጥቷታል ። አንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ደግሞ ውሳኔውን እናስቀለብሳለን እያሉ ነው ። የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው የእስራኤልን አቋም መደገፍ የአሜሪካንንም ሆነ የእሥራኤልን እሴቶች እንደመቃረን የሚቆጠር ነው ብለዋል ። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic