የአሜሪካን መንግስት እንደራሴዎችና ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ያለዉ የፖለቲካ ሁኔታ እንዳሳሰባቸዉ ገለፁ።
ይህ የተሰማዉ ባለፈዉ ሳምንት መገባደጃ የአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሜሪካንን የአፍሪቃ ፖሊሲ በገመገመበት ስነስርዓት ላይ ነበር። በተለይ በምክር ቤቱ የአፍሪቃ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር እንደራሴ ዶናልድ ፔይን የኢትዮጵያ መንግስት ወደአምባገነንነት ማምራቱና የወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ ሁኔታ እጅጉን እንዳሳሰባቸዉ አመልክተዋል።
አበበ ፈለቀ ፤ ሸዋዬ ለገሠ ሂሩት መለሰ