የአልሸባብ ግስጋሴና የኢትዮዽያ ምላሽ | ኢትዮጵያ | DW | 13.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የአልሸባብ ግስጋሴና የኢትዮዽያ ምላሽ

ኤልበርዴ ከኢትዮዽያ ድንበር ብዙም የማትርቅ የሰሜን ሶማሊያ ከተማ ናት። ደካማው የሶማሊያ መንግስት ለወታደራዊ ስልጠና የሚጠቀማት ቁልፍ ይዞታ ናት። ባለፈው ቅዳሜ በአልሸባብ እጅ ላይ ወደቀች።

default

ኤልበርዴ ከኢትዮዽያ ድንበር ብዙም የማትርቅ የሰሜን ሶማሊያ ከተማ ናት። ሮይተርስ የአልሸባብ የጦር አዛዥን ጠቅሶ እንደዘገበው በኤልበርዴ የመንግስቱ ጦር የለም። አዛዡ ሼክ ሀሰን ሞ አሊም ታኮው እንደገለጹት አልሸባብ በከባድ መሳሪያ ከደበደባት ኤልበርዴ የመንግስቱ ጦር ብዙም አልቆየም። ወደ ኢትዮዽያ ድንበር ዘልቀው ገብተዋል ። የኤልበርዴን መያዝ የኢትዮዽያ መንግስት ተራ ፕሮፖጋንዳ ሲል አጣጥሎታል። የኮሚኒኬሽንስ ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል አልሸባብን ለማግዘፍ ተብሎ የተፈበረከ ወሬ ብለውታል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic