የአለም የጦር መሳሪያ ሽያጭ | ዓለም | DW | 20.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የአለም የጦር መሳሪያ ሽያጭ

የስቶኮልም አለም አቀፍ የሰላም ምርመር ተቋም በምህፃሩ SIPRI የአለም አቀፍ የጦር መሳሪያዎችን ሽያጭ አስመልክቶ ትናንት አንድ ዘገባ አውጥቷል። በዘገባው መሰረት በአለም የጦር መሳሪያ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

የስቶኮልም አለም አቀፍ የሰላም ምርመር ተቋም በምህፃሩ SIPRI የአለም አቀፍ የጦር መሳሪያዎችን ሽያጭ አስመልክቶ ትናንት አንድ ዘገባ አውጥቷል። በዘገባው መሰረት በአለም የጦር መሳሪያ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።

በተለይ ወደ ሰሜን አፍሪቃዊ አገሮች እና ወደ ሶሪያ በርካታ መሳሪያዎች ተሸጠዋል። የተባበቱት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀው ከአለፈው አመት ጀምሮ በሶሪያ በሚካሄደው አመፅ የ8000 ሰዎች ህይወት የጠፋው ሩሲያ ለሶሪያ መንግስት በሸጠቻቸው የጦር መሳሪያዎች ነው። የአገሪቱ መንግስት ባለፉት አምስት አመታት 72 ከመቶውን የጦር መሳሪያ ከሩሲያ እና ኢራን ገዝቷል። የሶሪያ የጦር መሳሪያዎች ግዢ በአሁኑ ሰዓት በ580 ከመቶ ከፍ ብሏል። ፒተር ቬዝማን - በስቶኮልም አለም አቀፍ የሰላም ምርመር ተቋም የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጉዳዮች ተንታኝ ናቸው። ስለ ጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ችግር ሲናገሩ።

Kampfpanzer vom Typ Leopard 2 in voller Fahrt auf einem Testgelände (undatierte Aufnahme). Die Bundesregierung hat einem «Spiegel»-Bericht zufolge erstmals die Lieferung schwerer Kampfpanzer nach Saudi- Arabien genehmigt. Der Bundessicherheitsrat habe vor wenigen Tagen den Weg für den Export von modernen «Leopard II»-Panzern in das autoritär geführte Land frei gemacht, berichtet das Magazin. Die Saudis hätten Interesse an mehr als 200 Exemplaren. Der deutschen Rüstungsindustrie winkt damit ein Milliardengeschäft. Foto: KMW dpa (ACHTUNG: Veröffentlichung nur mit Angabe der Quelle Krauss-Maffei Wegmann) (zu dpa 0862 «Spiegel»: Deutscher Panzer-Export nach Saudi-Arabien genehmigt am 03.07.2011) +++(c) dpa - Bildfunk+++

ሊዮፓርድ ሁለት

« ችግሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እና ወታደራዊ መገልገያዎች መጠቀሙ ላይ ነው። ግልጽ ነው የጦር መሳሪያዎች ካሉ ተቃውሞ ሰልፈኞች ላይ ይተኮሳሉ። ራዳር ካለ የተቃውሞ ሰልፈኞች እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ሲባል መጠቀም ይቻላል። እንደዚህ አይነት የወታደራዊ መገልገያዎች ሳይቀሩ አምባገነን መንግስት እንዲቆይ ይረዳሉ።»

እኢአ ከ 2007 እስከ 2011 ዓ ም ባሉት 5 አመታት ውስጥ የአለም የጦር መሳሪያዎች ንግድ በ24 ከመቶ ከፍ ብሏል። 44 ከመቶ በዋንኛነት ፣ ወደ እስያ እና ፓሲፊክ ፤ በሁለተኛ ደረጃ - 19 ከመቶ ወደ አውሮፓ! ከዛ ቁጥሩ ትንሽ ዝቅ በማለት ወደ መካከለኛ ምስራቅ 17 ከመቶ ያክል ተሸጧል።

መሸጥ እና መግዛት በተከለከለበት ወቅት እንኳን ሞስኮ ህጉን በመጣስ የጦር መሳሪያ አቅርቦቷን አላቋረጠችም ይላሉ ተንታኙ። ለዚህም ሩሲያ የሰጠችው ምላሽ ሶሪያ ከውጪ ለሚደርስባት ማስፈራሪያ የጦር መሳሪያ ያስፈልጋታል ስትል ነው። ባለፈው አመት ሊቢያ ውስጥ የጋዳፊ መንግስት የተጠቀማቸው የጦር መሳሪያዎችም ቢሆኑ ከብሪታኒያ እና ከፈረንሳይ የተገዙ ናቸው ይላሉ ተንታኙ። ከሲፕሪ የአውሮፓን የጦር መሳሪያዎች ሽያጭ በተመለከተ ማርክ ብሮምሊ ሲናገሩ፤ « ጥያቄው እንደ ጦር መሳሪያ አቅራቢ ምን ያህል ለአደጋ ለመጋለጥ ዝግጁ ነኝ የሚለው ነው። አውሮፓ ውስጥ የሽያጭ መመሪያዎቹ የወጡት መሳሪያውን ለምን መጠቀም አስፈለገ የሚለው ነው እንጂ መሳሪያውን ለምን መጠቀም ይቻላል የሚለው አይደለም።»

A Syrian army tank is seen in Yabroud near Damascus March 8, 2012. Picture taken March 8, 2012. REUTERS/Shaam News Network/Handout (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST MILITARY) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS

በሶሪያ በሚካሄደው አመፅ

አቢዮቱ እንደ አንዳንድ የሰሜን አፍሪቃ አገሮች አይፈንዳ እንጂ፤ ሌሎች አገሮችም መሳሪያ እየካበቱ ነው ይላሉ ተንታኝ ቬዜማን። ከነዚህም አገሮች መካከል አልጄሪያ እና ሳውዳረቢያ ይገኙበታል። ሳውዳረቢያ ባለፉት 20 አመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የጦር መሳሪያዎች ሸምታለች። የሳውዳረቢያ መንግስት በ29 ቢሊዮን ዶላር 84 አዳዲስ እና 70 ዘመናዊ የሆኑ የጦር አይሮፕላኖች ከዮናይትድ እስቴትስ ገዝታለች።

የሲፕሪ ዘገባ ጀርመን ባለፈው አመት አልጄሪያን የጦር ታንኮች እንደምትሸጥላት ቃል መግባቷን ጠቅሷል። ሲፕሪ በዘገባው አያካተው እንጂ ሊዮፓርድ ሁለት በመባል የሚታወቀውን 200 መድፎች ጀርመን ለሳውዳረቢያ ለመሸጥ አስባለች የሚለው ዜና በጀርመን ሲያነጋግር ሰንብቷል። ጀርመን በጦር መሳሪያ ንግድ ከአለም የ3ኛነትን ስፍራ ይዛለች። መሳሪያዎቹን ለምንም ይጠቀሙበት ለምን፤ ዲሞክራሲ ባልሰፈነባቸው አገሮች መሸጥ እራሱን የቻለ ችግር ነው ይላሉ፤ የመካከለኛው ምስራቅ ተንታኝ ቬዜማን፤

«ለአንድ አገር የጦር መሳሪያ ካቀረብክ ፤በተቀባዩ አገር እንደ ድጋፍ ሊታይ ይችላል። ለአንድ አምባ ገነን የጦር መጣሪያ ካቀረብክ ፤ አምባ ገነኑ በመርህ ደረጃ የሚያምነው በርግጠኝነት እሱን እንደምትደግፍ ነው። »

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 20.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/14N4q
 • ቀን 20.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/14N4q