የኒውዮርክ፣የተቃውሞ ሰልፍ በ«ዎል እስትሪት» | ዓለም | DW | 04.10.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኒውዮርክ፣የተቃውሞ ሰልፍ በ«ዎል እስትሪት»

«ወል እስትሪትን፣ በቁጥጥር ሥር አውሉ!» በሚል መፈክር ሲካሄድ የሰነበተው የተቃውሞ ሰልፍ ምንም እንኳን 700 ግድም የሚሆኑ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር ቢውሉም ሰልፉ ቀጥሏል።

default

ኒውዮርክ

እንደውም በሌሎች የ ዩ ኤስ አሜሪካ ታላላቅ ከተሞችም ሰልፉ ተስፋፍቶዋል። በቺካጎ፣ ቦስተን እና ሎስ አንጀለስ በመቶዎች የሚቆጠሩ በየመዘጋጃ ቤቶች ፍለፍት የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው። ተሸጥን እያሉ ነበር የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ትናንት በቦስተን ድምፃቸውን ሲያሰሙ የዋሉት። ተቃውሞአቸው ያተኮረው በባንኮች ላይ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በማኅበራዊ ኑሮ ፍትኀዊነት መጓደል ላይ ነው። አኒካ ክሬምፕል ከተቃውሞ ሰልፈኞቹ ጋር ተነጋግራለች።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic