የችግኝ ተከላ እና የአድማጮች አስተያየት | ጤና እና አካባቢ | DW | 25.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የችግኝ ተከላ እና የአድማጮች አስተያየት

የክረምት ወራትን ጠብቆ የዛፍ ችግኞችን መትከል የተለመደ ነዉ። ዛፎች ከባቢ አየር ዉስጥ የተከማቸዉን አደገኛ ጋዝ ለራሳቸዉ ተፈጥሯዊ ምግብ ማዘጋጃነት በመጠቀም አየሩን ከማፅዳታቸዉ በተጨማሪ የአካባቢን አየር ንብረት ሚዛን ለመጠበቅ እንደሚረዱ ሳይንሱ ያወሳል።

Nepalesische Schüler pflanzen Bäume

ለዚህም በብዛት ዛፎችን መትከል ይገባል በሚል የሚበረታታዉ። ዛፎችን የመትከሉ አስፈላጊነት ቢታመንም በዘመቻ በሚከናወኑ የችግኝ ተከላዎች የሚተከለዉን ብዛት ያህል ለዉጤት አለመብቃታቸዉ ብዙዎች የሚያነሱት እዉነት ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት 3 ቢሊዮን ችግኝ በዘንድሮዉ ክረምት ተተከለ መባሉን በማስመልከት ያቀረብነዉን ዝግጅት ስናጠናቅቅ እናንተ አድማጮቻችን በየአካባቢዎቻችሁ ያስተዋላችሁትን እንድታካፍሉን ጋብዘን ነበር። ከአርባ የሚበልጡ አድማጮችም በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ አስተያየታቸዉን አስፍረዋል። በድምፅም አስተያየታቸዉን የሰጡን አሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic