ቻይና በጅቡቲ የከፈተችዉ የጦር ሰፈር ከዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሰፈር በቅርብ ርቀት መገኘቱ ዋሽንግተንን እንዳሳሰበ የሚገልጸዉን ዘገባ አሜሪካን አስተባበለች። ለዶቼ ቬለ የአሜሪካን የመከላከያ ሚኒስቴር የአፍሪቃ እዝ ክፍል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሰጡት ምላሽ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ከቻይና ጋር በሁለትዮሽ ትብብር እንደሚሠሩ አመልክተዋል።
የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ አክለዉም ሁለቱ ሃገራት አክራሪነትን እና ሕገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን ለመከላከል የጋራ ፍላጎት እንዳላቸዉም ገልጸዋል። አንድ የኤኮኖሚ ምሁር በበኩላቸዉ የቻይና ትኩረት ንግዱ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ በዚህ ላይ ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ