የትንኝ ስጋት በደቡብ ወሎ | ጤና እና አካባቢ | DW | 15.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የትንኝ ስጋት በደቡብ ወሎ

ደቡብ ወሎ ዉስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች አንዲት በራሪ ፍጥረት «የአካባቢዉ ሰዎች ትንኝም ጢንዚዛም እያሉ ይጠሯቷል፤» በሰዉነት ላይ ባለ የትኛዉ ቀዳዳ ገብታ ጤና እንደምታዉክ እየተነገረ ነዉ። ይህ ጥቆማ ወደ ዝግጅት ክፍላችን ከአንድ በሚበልጡ አድማጮች ነዉ የተላከልን።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:59

የባህል ወይስ ዘመናዊ ህክምና

 እነሱ እንደሚሉት በደቡብ ወሎ አምባሰል በሚገኙ አካባቢዎች በብዛት ትንኝ ወይም ጢንዚዛ ያሏት በራሪ ፍጥረት በበርካታ ሰዎች ጆሮ ዉስጥ ገብታ ሰዎቹ ተቸግረዋል። በዘመናዊ ህክምና እርዳታ ማግኘት ስለማይችሉም ለማስወጣት ባህላዊ መድኃኒት አድራጊዎች ጋር መሄድ ይኖርባቸዋል። ስለሚባለዉ ነገር ሰምተናል ከሚሉ አንስቶ፤ ሊወጣላቸዉ ወደ ባህል ህክምና አዋቂዎች ዘንድ የመጡትን አይተናል አነጋግረናል የሚሉም አሉ። በተቃራኒዉ የጆሮ ህክምና ባለሙያ የሆኑ አንድ ሀኪም ደግሞ ጉዳዩ የስነልቡና ችግር እንደሆነ  ይህን የሚሉትን ችግር ማለትም ስለአንድ ጉዳይ እያሰቡ ያ እንደሆነ አድርጎ ማመን እና ያንንም ብዙዎች አምነዉ የዚያ ሃሳብ ተጋሪ እንዲሆኑ የሚያበቃ መዘዝ እንዳይከተል ለጤና ቢሮዉ ጠቁሜ ነበርም ይላሉ። የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ጉዳዩን ከኅብረተሰቡ መስማቱን፤ እንዲያጣራም ሀኪሞች የተካተቱበት ቡድን ማሰማራቱን ይናገራል። ከሚወራዉ ያለፈ ግን በተጨባጭ በባህል ህክምናዉ ወጥቶ የታየ ትንኝም ሆነ ጢንዚዛ የለም ነዉ የሚለዉ የጤና ቢሮዉ። መንስኤዉ እየተጣራ ሲሆን ለኅብረተሰቡ ሊሰጥ የሚችለዉ የዘመናዊ ህክምና ምን ሊሆን እንደሚችልም አብሮ እየተመረመረ መሆኑንም አስረድቷል። ዋናዉ ነገር እስካሁን በዚህ ችግር የሰዉ ህይወት አላለፈም። ይህም እማኝነን በሚሉትም ሆነ በጤና ቢሮዉ ባለስልጣን ተገልጿል። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic