የኩርድ ሠራተኞች ፓርቲ PKK አማፅያን ቱርክ ዘልቀዉ በወታደራዊና ፖሊስ ሰፈሮች ከባድ ጉዳት ካደረሱ ወዲህ የሁለቱ ወገኖች ግጭት አገርሽቷል።
ቱርክ 26 ወታደሮች ከተገደሉባት በኋላ ወደሰሜን ኢራቅ ወታደሮቿ ድንበር ዘልቀዉ በመግባት በኩርድ አማፅያን ይዞታ ላይ ጠንካራ የአፀፋ ጥቃት እንዲሰነዝሩ አዝምታለች። የተመድ ዋና ጸሐፊና የአዉሮጳዉ ኅብረት የአማፅያኑን ርምጃ ተቀባይነት የለዉ ሲሉት፤ በዋና ከተማ አንካራ ለሰልፍ የወጡ በሺዎች የተገመቱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም አማፅያኑ ያደረሱትን ጥቃት አዉግዘዋል።
ቶማስ ቦርማን
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሠ