የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመፍትሔ ፍለጋ ጥሪ | ኢትዮጵያ | DW | 06.10.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የተቃዋሚ ፓርቲዎች የመፍትሔ ፍለጋ ጥሪ

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካዊ  ሁኔታ በተመለከተ በሀገሪቱ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በየጊዜው  በሚያወጡዋቸው ጽሁፎች እና በሚሰጡዋቸው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ለሕዝቡ መረጃ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53

የመኢአድ እና የመድረክ ጥሪ


የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ በምህፃሩ «መ ኢ አ ድ» ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለው፣  ህብረተሰቡ መንግሥት የሚፈፅመው የእንግልት፣ የእስር እና የግድያ ፣ ባጠቃላይ የመብት ጥሰት ሰለባ በመሆኑ ጥሰቱ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት፣ ተጠያቂውም በሕግ መጠየቅ አለበት። የመኢአድን ሀሳብ በመሰረቱ የሚጋራው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ እና መኢአድ ለፖለቲካዊ ችግሮች መፍትሔ የሚያፈላልግ  ሁሉንም ወገኖች የሚያሳትፍ ድርድር እንዲካሄድም ጠይቀዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic