የተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ መኖር አለመኖር አወዛገበ  | ኢትዮጵያ | DW | 12.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ መኖር አለመኖር አወዛገበ 

በሚያቀርባቸዉ ጽሑፎቹና ሃሳቦች ጥፋተኛ ተብሎ የሦስት ዓመት እስር የተፈረደበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ፤ ቤተሰቦቹ የተለያየ ፍርድ ቤት ቢፈልጉትም የለም እየተባሉ መመለስ ከጀመሩ ስድስተኛ ቀን እንደሞላቸዉ ለዶይቼ ቬለ ገለጹ።

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉና ስማቸዉና ማዕረጋቸዉን መግለፅ እንዳልፈለጉ የተገለጸዉ  አንድ የዝዋይ ማረሚያ ቤት ባልደረባ ግን «የለም የሚባል ነገር የለም፤ ታራሚዉ  እኛ ጋር ነዉ፤ እንደማንኛዉም ታራሚ በክፍሉ ይገኛል።» ሲሉ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ   ከሦስት ዓመት እስር በኋላ ባለፈዉ ጥቅምት 3 ቀን በአመክሮ ይፈታል ተብሎ ቢጠበቅም ከእስር አለመዉጣቱም ተገልጿል።  


ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር 


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic