የቦምብ ፍንዳታ በአንዋር መስጊድ | ኢትዮጵያ | DW | 11.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቦምብ ፍንዳታ በአንዋር መስጊድ

አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የየዓይን ምስክር ጠቅሶ ሮይርስ እንደዘገበው ሶስት ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አይቷል ። የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ግን ገና በውል አለመታወቁን አመልክተዋል ።

በአዲስ አበባው የአንዋር መስጊድ ዛሬ የተወረረ የእጅ ቦምብ ቢያንስ 6 ሰዎችን ማቁሰሉ ተዘገበ ። ጥቃቱ የደረሰው መርካቶ በሚገኘው በዚሁ መስጊድ ዛሬ ከተካሄደ የየፀሎትና የስግደት ስርዓት በኋላ ነበር ። አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ የየዓይን ምስክር ጠቅሶ ሮይርስ እንደዘገበው ሶስት ከባድ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች አይቷል ። የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር ግን ገና በውል አለመታወቁን አመልክተዋል ።ለጥቃቱ ተጠያቂ የሆነውም ወገን ገና አለመታወቁን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ