የብሪታኒያ ካሳ ለቀድሞ የዋንታናሞ ዕስረኞች | ዓለም | DW | 17.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የብሪታኒያ ካሳ ለቀድሞ የዋንታናሞ ዕስረኞች

የብሪታኒያ መንግስት ለቀድሞ የዋንታሞ ዕስረኞች ካሳ ለመክፈል መወሰኑን ትናንት አስታውቋል ። መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውም በእስር ላይ ሳሉ በደል ደርሶብናል ሲሊ ከከሰሱ የቀድሞ እስረኞች ጠበቆች ጋር ለሳምንታት ከተካሄደ ድርድር በኃላ ነው ።

default

ብንያም ሞሀመድ

ከፍርድ ቤት ውጭ በተካሄደ በዚሁ ስምምነት መሰረት መንግስት ለተበዳዮቹ ከ1 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም ከ 1.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ ይከፍላል ። ከፍተኛው ካሳ ከሚያገኙት ከሳሾች ውስጥ የብሪታኒያው ነዋሪ ኢትዮጵያዊው ብንያም ሞሀመድ አንዱ መሆኑን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ዘግቧል ።

ድልነሳ ጌታነህ ፣ ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ