የባሊው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ | ዓለም | DW | 14.12.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የባሊው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ

የባሊው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል።የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩ ተወዳዳሪ እና የዘንድሮ የአካባቢ ጥበቃ የኖቤል ተሸላሚ አል ጎር ሐሙስ ታህሳስ ሶስት በባሊው ጉባኤ ላይ አሜሪካንን አስመልክተው ንግግር ሲያደርጉ ከፍተኛ በሆነ ድጋፍና ጭብጨባ ታጅበው ነበር።

ባሊ ኢንዶኔዢያ

ባሊ ኢንዶኔዢያ

የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በቦታው ላይ ተገኝተዋል።የፓትሮል መኪኖች አብረዋቸው የሉም።በአራት ጠባቂዎቻቸው ብቻ ታጅበው በእግራቸው ወደ አዳራሹ አቀኑ።አሜሪካዊው የአካባቢ ጥበቃ የዘንድሮ የኖቤል ተሸላሚ አል ጎር።አዳራሹ ውስጥ የተሰበሰበው ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ ታዳሚ ሞቅ ባለ መንፈስ ተቀበላቸው።

አልጎር ንግግር ከማድረጋቸው በፊት ሰኞ ኖርዌይ ኦስሎ ላይ የሠላም ኖቤል ተሸላሚና የዓለም አካባቢ ጥበቃ ኃላፊ ለሆኑት ህንዳዊው ራሼንድራ ፓሳውሪን ሠላምታ አቀረቡ።ከዚያም የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ አገራቸው የያዘችውን አቓም በመንቀፍ ንግግራቸውን ጀመሩ።

በመሰረቱ አልጎር ለዓለም የአካባቢ ጥበቃ አንግበው የተነሱትን የተቀደሰ ዓላማ እንዲገፉበት የሚያበረታቱ አራት መቶ ሺህ የኤሌክትሮኒክስ መልዕክቶች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ደርሷቸዋል።በእርግጥም አሁን ዓለም ትኩሳት ላይ ነው ያለችው።እናም ከባሊው የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ አንዳች ማረጋገጫ ይጠበቃል።

የአውሮጳ ህብረት እ.ኤ.አ. እስከ ሁለት ሺህ ሃያ ዓ.ም. ድረስ የአካባቢ አየር በካይ ጋዞችን ከሃያ አምስት እስከ አርባ በመቶ መቀነስ የሚያስችል ዕቅድ ለጉባኤው አቅርቧል።አሜሪካ በዋናነት ከግዙፍ ኢንዱስትሪዎችዋ የሚለቀቁትና አካባቢን የሚበክሉ አደገኛ ጋዞቹዋን በተባለው መጠንና ግዜ ለመቀነስ ፍላጎት የላትም።ይህም በመሆኑ ጉባኤው በውጥረት ተይዟል።ሆኖም አንዳንድ ምንጮች እንደገለጹት የአሜሪካና የአውሮጳ የአከባቢ ጥበቃን አስመልክቶ የገቡበት ፍጥጫ በሰከነ መልኩ በመልካም ውጤት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።