1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የበርኑ ድንቅ ክስተት

ዘንድሮ ጀርመን ህገ መንግስቷን ያረቀቀችበት ስድሳኛ አመትን ምስራቅና ምእራብ ጀርመን የተቀላቀሉበት ሃያኛ አመትን በማዉሳት ላይ ትገኛለች። ከሁለተኛ አለም ጦርነት በሓላ ጀርመን ለመጀመርያ ግዜ የአለም የግር ኻስ ጨዋታ ግጥምያ አሸናፊ የሆነችበት አመት እግር ኻስ ባህሉ ለሆነዉ ጀርመናዊ ታላቅ ታሪክን አስቀምጦለት ነዉ ያለፈዉ

default

የአሸናፊነት ደስታ

እ.አ 1954 አ.ም ጀርመን አለም አቀፍን የእግር ኻስ ጨዋታ ግጥምያ አሸናፊ በሆነችበት ደቂቃ የእግር ኻስ ዉድድሩን ጨዋታ በራድዮ በቀጥታ ለአድማጮች ያስተላልፍ የነበረዉ ጋዜጠኛ በደስታ ጎል ጎል እያለ ደስታዉን ሲገልጽ፣ የሰማ አሁንም የበርኑ ድንቅ ክስተት ይላል። ጀርመን በያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት ህገ መንግስቷን ያጸደቀችበት ፊደራል ሪፕሊክ ጀርመን የተመሰረተበትን ስድሳኛ አመት፥ እንዲሁም ምስራቅና ምእራብ ጀርመን የተቀላቀሉበትን 20ኛ አመትን ስታከብር የታሪክ ማህደሯን በመግለጥ የተለያዩ ክስተቶችን ትቃኛለች። አምስተኛዉን የአለም እግር ኻስ ዋንጫ ያሸነፈችበት ሁኔታም አንዱ በታሪክ ማህደሯ ከተመዘገቡት ሁኔታዎች ሆንዋል። በዚህ በጀርመን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ይህንን ታሪካዊ ሁኔታ ሲታወስ በተለይ የአምስተኛዉ የአለም አቀፍ የእግር ኻስ ጨዋታ ሳይታወስ የሚቀር አይደለም።"እ.አ 1954 አ.ም ጀርመን አለም አቀፍን የእግር ኻስ ጨዋታ ግጥምያ አሸናፊ በሆነችበት ደቂቃ የእግር ኻስ ዉድድሩን ጨዋታ በራድዮ በቀጥታ ለአድማጮች ያስተላልፍ የነበረዉ ጋዜጠኛ በደስታ ጎል ጎል እያለ ደስታዉን ሲገልጽ፣ የሰማ አሁንም የበርኑ ድንቅ ክስተት ይላል
እ.አ 1954 አ.ም በስዊዘርላንድ በርን ከተማ የተካሄደዉ 5ኛዉ የአለም የእግር ኻስ ግጥምያ ዉድድር በተለይ በጀርመናዉያኑ ዘንድ የበርኑ ድንቅ ክስተት በመባል በታሪክ እና በባህል ማህደር ተመዝግቦ ይገኛል። ጀርመን ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት አገግማ እ.አ 1954አ.ም ለመጀመርያ ግዜ የአለም የእግር ኻስ ግጥምያ የዋንጫ አሸናፊ ስትሆን ህዝብዋ በጦርነት ያጣዉን ጉልበት እና በራስ ያለመተማመን ገጽታ እንደጋና ያገኘበት፣ አንገቱን ያቀናበት ድል ነዉ ሲሉ በክብር ያስቡታል።
በወቅቱ ከበርን በራድዮ ጨዋታዉን በቀጥታ በራድዪ ሲያስተላልፍ የነበረዉ ጀርመናዊ ጋዜጠኛም
«በመከታተል ላይ ያላችሁት ስርጭት በርን ከተማ በሚገኘዉ ቫንክ ዶርፍ ስታዲዮም በጀርመን እና በሃንጋሪ መካከል በመካሄድ ላይ ያለዉን የአለም እግር ኻስ ጨዋታ የዋንጫ ጕጥምያን ነዉ።»
ሃምሌ 4 ቀን 1954 አ.ም አሁንም እንደ አዉሮጻዉያኑ አቆጣጠር ነዉ በስዊዘርላንድ ስድስት ከተሞች ለሁለት ሳምንት ተኩል የዘለቀዉን የእግር ኻስ ጨዋታ ግጥምያ ጀርመናዉያኑ ማጣርያዉን አልፈዉ ለዋንጫ ግጥምያ ከሃንጋሪ ጋር ለመጋጠም ሲደርሱ 890,000 ያህል ህዝብ በቀጥታ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾች ደግሞ ጨዋታዉን በቴሌቭዥን እንደተከታተሉት ተዘግቦአል። ይህ ጀርመን ለመጀመርያ ግዜ ለአለም የእግር ኻስ ጨዋታ ለዋንጫ ግጥምያ የቀረበችበት ጨዋታም በጀርመን ለመጀመርያ ግዜ ነበር በቴሌቭዥን በቀጥታ ለተመልካች የቀረበዉ። የራድዮ ጋዜጠኛዉ
«ጀርመን የዋንጫዉን ለመዉሰድ የሚያስችለዉን ግጥምያ ለመሳተፍ ደርሳለች። እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ራሱ አንድ ትልቅ ድል ነዉ። አንድ ትልቅ የእግር ኻስ ግጥምያ ድል! ለዚህ ደግሞ ለመድረስ የበቃነዉ ምስጋና ልናቀርብላቸዉ የሚገባን ብሄራዊ ተጫዎቾቻችን ስለ እግር ኻስ ጨዋታ የጠለቀ እዉቀት እና ጥበብ ስላላቸዉ ነዉ።»

Deutschland Geschichte Kultur Fußball WM 1954ጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ በራድዮ የጨዋታዉን ሲያስተላልፍ የደስታ ስሜት በተሞላበት መንፈስ ነበር። ምንም እንኻ የሃንጋሪዉ የእግር ኻስ ቡድን በጨዋታዉ ወቅት ኻስዋን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እያጠቃ ቢቆይም «ሊብሪሽ ጥሩ እየተጫወተ አይደለም. ሃንጋሪ እያጠቃ ነዉ። ሃንጋሪያዊዉ አጥቂ Kocsis ካስዋን ለጋ የቡድኑ አንበል ኻስዋን አግኝቷል ሊለጋ ነዉ ለጋ... ጎል» ጨዋታዉ ከተጀመረ ስምንት ደቂቃ ሆኖታል ሃንጋርያዉያኑ ሁለት ለዜሮ እየመሩ ነዉ። በሁለተኛዉ አለም ጦርነት ጀርመን የጠፋዉን ስሟን በማደስ በስፖርታዊዉ የግጥምያ ዉድድር ለዋንጫ መቅረብዋ እራሱ ህዝቡዋን አኩርቶታል አንገቱንም ቀና አድርጎታል ምንም እንኻ ገና ጨዋታዉ ከመጀመሩ ሽንፈት ቢደርስበትም ጨዋታዉን በቀጥታ በመከታተል በራድዮ ያስተላልፍ የነበረዉ ጋዜጠኛም እንዲሁ ነበር የገለጸዉ
«ያም ሆነ ይህ ይንን ግጥምያ ቡድናችን ቢሸነፉም፣ ተጨዋቾቻችን ድንቅ የሆነ ጨዋታን አሳይተዋል ብዪ ነዉ የማስበዉ።»
ጨዋታዉ ሁለት ለዜሮ በሃንጋሪ መሪነት ቀጠለ ከረፍት መልስ ጀርመን ሁለት ግብ በማስቆጠር እስከ ሰማንያራተኛዉ ደቂቃ ግቡን አጥሮ ቆየ የሃንጋሪዉም ቡድን ጠንካራ ጨዋታን እያሳየ ነዉ። ጨዋታዉ ሊጠናቀቅ አምስት ስድስት ደቂቃ ቀርቶታል። በቴሌቭዥን እና በራድዮ ከስዊዠርላንድ በርን ከተማ ከሚገኘዉ ስታድዮም የሚከታተለዉ ጀርመናዊ ነፍስ ዊች ነፍስ ግቢ አይነት ሁኔታ ጨዋታዉን በመከታተል ላይ ነዉ። ዚመር ማን የተባለዉ ጋዜጠኛም ጨዋታዉን በመከታተል ለራድዮ ታዳሚዎቹ ስሜቴን መያዝ መቆጣተር አልቻልኩም የቀረን ስድስት ደቂቃ ነዉ ይላል ኻስዋ ጀርመናዊያኑ ጋር ትገኛለች! ቀጠለ ዘገባዉን
«እና Bozsik የያዘዉን ኻስ በጀርመኑ ተጫዋች በሼፈር ተነጥቆአል። ሼፈር በጭንቅላት አብርዶ የያዛትን ኻስ ለራን አሳልፎ ሰጥቶታል! ራን ኻሷን መለጋት አለበት፣ ራን ለጋ ጎል! ጎል! ጎል!
ሶስት ለሁለት ጀርመን እየመራ ነዉ። ጨዋታዉ ሊፈጸም አምስት ደቂቃ ነዉ የቀረዉ፣ ያሰጋል ያሰጋል .......በጣም ጭንቀት ላይ ነኝ» እንደገና አሁንም ጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ በመቀጠል
«የሃንጋሪዉ ተጫዋች Kocsis ኻስዋን እያንከባለለ ነዉ። ብቻ የደከመ ይመስላል። ካስዋን በግራ ክንፍ ይዞ ለማለፍ እየሞከረ ነዉ ጀርመኑ ተጫዋች ሼፈር ካስዋን ነጥቆ ወደ ፊት አልፋል። ለሊንግ አቀበለዉ ሊንግ ለማለፍ እየሞከረ ነዉ.... እንደገና ለሼፈር አቀብሎታል ሼፈር አልፎአል .... ራን ኻስዋን እየጠበቀ ነዉ ... ራን ኻስዋን አግኝቶአል ራን መታ .... ጎል ጎል»
ሰማንያ አምስተኛዉ ደቂቃ ላይ ሼፈር የተሰኘዉ ጀርመናዊ ተጫዋች ለራን አቀብሎት ራን ካስገባ በኻላ ጀርመን ሁለት ለሶስተ መምራቱን ቀጠለ። ዚመር ማን የተባለዉ ጋዜጠኛ ጨዋታዉን በመከታተል ስርጭቱን ቀጥሎአል። ይጮሃል! ይቅርታም ይጠይቃል! የቀረን አራት ደቂቃ ነዉ አራት ደቂቃ ነዉ! አበድክ አትበሉኝ፣.. ይቅርታ አድርጉልኝ ይላል ጨዋታዉ ቀጠለ። ጀርመን ግብ አካባቢ ሃንጋሪ የእጅ ዉርወራ አገኘች ጀርመናዊዉ ጋዜጠኛ ቀጠለ ዘገባዉን
«ሃንጋሪ የእጅ ዉርወራ አግኝታለች፣ ካስዋን Bozisk ሊወረዉር ነዉ። ..... አልቋል... ተጠናቋል ጨዋታዉ ተፈጸመ። ጀርመን የአመቱን የአለም የእግር ኻስ ጨዋታ አሸናፊ ሆናለች። ጀርመን ሃንጋሪን ሶስት ለሁለት በማሸነፍ ዘንድሮ በበርን ከተማ የተካሄደዉን የአለም የግር ኻስ ጨዋታ አሸናፊ ሆናለች»

Deutschland Geschichte Kultur Fußball WM 1954 Fritz Walter


ጨዋታዉ ተፈጽሞ ጀርመን ዋንጫዉን ቤትዋ ለማስገባት በቃች። ከሁለተኛዉ አለም ጦርነት በኻላ በአለም አቀፍ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ የጀርመን ባንዲራ ከፍ ብሎ ተዉለበለበ፣ ትክክለኝነት አንድነት፣ ነጻነት የሚል ትርጓሚ ያለዉ የጀርመኑ ብሄራዊ መዝሙር ከፍሎ ተዘመረ። ጋዜጦች በወኔና በድፍረት «ትከክለኛዉን ትግል እስከ ሚችሉት ድረስ ተጋድለዉ አሳዪ» ሲሊ የጀርመንን ብሄራዊ የግር ኻስ ቡድን በማድነቅ አወደሱ። ከጦርነቱ ወዲህ ጀርመናዉያን ለመጀመርያ ግዜ ያገር ፍቅራቸዉን በግልጽ አሳዩ።
እ.አ 1954 : 1974 እና 1990 አ.ም ጀርመን የአለም የእግር ኻስ ጨዋታን አሸናፊ ስትሆን በ 2006 አ.ም ማለት የ 18 ኛዉን የለም የግር ኻስ ጨዋታ አዘጋጅ ሆናም ነበር። በዚህ የአለም ህዝቦች በጀርመን እንግድነት የተባለለት የ18ኛዉ የአለም የግር ኻስ ጨዋታም የሶስተኛነትን ቦታ መያዝዋ ይታወሳል።
ዘንድሮ ጀርመን ህገመንግስቷን ያጸደቀችበት ስድሳኛ አመትን እንዲሁን ምስራቅ እና ምእራብ ጀርመን አንድ የሆኑበትን ሃያኛ አመት ስታከብር በዚህ አታት የተሰሩትን ታሪኮች ታወሳለች ታድያ ጀርመን በ 1954አ,ም የተካሄደዉ 5ኛዉ የአለም የግር ኻስ ጨዋታ አሸናፊ የሆነችበት ዘመን፣ እግር ኻስን ባህሉ ያደረገዉ ህዝቧ የታሪክ ማህደሩን በማገላበጥ ያወሳዋል።