የበረራ ቁጥጥርና የእስራኤል ልምድ | ዓለም | DW | 08.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የበረራ ቁጥጥርና የእስራኤል ልምድ

የቀናዉ ወረፋ ከያዘበት ጣጣዉን ጨርሶ የጉዞ መቆጣጠሪያዉን እስኪያልፍ (ቼክ-ኢን) ድረስ በትንሹ አንድ ሠአት ያስፈልገዋል።ያዉም እድለኛ ከሆነ

default

የአካል መፈተሻ

07 01 10

ዴትሮይት ላይ የመንገደኞች አዉሮፕላን ለማጋየት የተደረገዉ ሙከራ ከከሸፈ ወዲሕ የበረራ ጥበቃን ለማጠናከርና የአሸባሪዎችን አደጋ ለመቀነስ በየአዉሮፕላን ማረፊያዉ የአካል መመርመሪያ መሳሪያ እንዲተከል በየሐገሩ የሚደረገዉ ዉይይት ተጠናክሯል።ግን ያለ አካል መመርመሪያ መሳሪያ መቆጣጠር ይቻላል።የእስራኤሉ የቤን ጉሪዮን አዉሮፕላን ጣቢያ ለዚሕ ማረጋገጪያ ነዉ።አዉሮፕላን ማረፊያዉ ሰዎች በአካል መሳሪያ ሳይፈተሹ አስተማማኝ ከሆኑት አዉሮፕላን ጣቢያዎች አንዱ ነዉ። ዘባስቲያን ኤንገልብሬሽት የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናክሮታል።

ቴል-አቪቭ።ቤን ጎሪዮን አዉሮፕላን ማረፊያ።የእስራኤል ትልቁ እና ብቸኛዉ አለም አቀፍ የበረራ መስመር ነዉ።ከአለም አስተማማኝ የአዉሮፕላን ጣቢያዎችም አንዱ።ከጉዞ መቆጣጠሪያ በር ላይ የሚቀመጡት ሥለላ ወይም የደሕንነት ሰራተኞች እያንዳዱን መንገደኛ ያነጋግራሉ።ይጠይቃሉ «ወዴት ነዉ-የሚጓዙት?»፥ «እስራኤል የነበሩት ለምን ነበር?»፥ «ሻንጣዉን የሽከፈዉ ማነዉ?» «እቃ የሰጠዎት ሰዉ አለ?»-እያሉ።ሌላም።

ጥያቄ መልሱ-አንዳዴ ረጅም ጊዜ ይፈጃል።አስራ-አምስት ደቂቃና ከዚያም በላይ።መርማሪዎቹ መንገደኛዉ የሰጠዉን መረጃ ትክክለኝነት ያጣራሉ።መታወቂያ፥ ደብዳቤ ወይም ሌላ የወረቀት ማረጋገጪያ ይጠይቃሉ።እኒያ ነጭ ሸሚዝና ቡላ ሱሪ ያጠለቁት ወጣት የደሕንነት ሠራተኞች መንገደኛዉን ከጠረጠሩት ጥያቄ-መልሱን አቋርጣዉ ሌላ ባልደረባ ምናልባትም አለቆቻቸዉን ያማክራሉ።

የመጨረሻዉ ተጠርጣሪ ማንነት እስኪጣራ ድረስ ጥያቄ-መልሱ ይቀጥላል።ከዚያ በሕዋላ ነዉ-እንግዲሕ ሻንጣዎች የፈንጂ ምልክትን በቅጡ በሚያሳይ ልዩ መሳሪያ የሚፈተሹት።አንዳዴ ከግማሽ ያሕሉ ሻንጣ እየተከፈተ በልዩ መሳሪያ ይበረበራል።መርማሪዎቹ በተለይ የወይራ ዘይት፥ማር፥ ማርመላት የመሳሰሉ ፈሳሽና ልቁጥ ነገሮችን ለረጅም አጥብቀዉ የመረምራሉ።

የቀናዉ ወረፋ ከያዘበት ጣጣዉን ጨርሶ የጉዞ መቆጣጠሪያዉን እስኪያልፍ (ቼክ-ኢን) ድረስ በትንሹ አንድ ሠአት ያስፈልገዋል።ያዉም እድለኛ ከሆነ።አይሁድ እስራኤላዉያን፥አዛዉንቶች እና ልጆች ባስከተሉ ቤተሰቦች ፍተሻዉን ፈጥኖ የመጨረሽ እድል አላቸዉ።


የስራኤል የቁጥጥር ፅንሠ-ሐሳብ ግልፅ ነዉ።የበረራ ደሕንነት ለመጠበቅ ከዘመናዊ ቴክኒክ ይልቅ ሰዉ የሚያደርገዉ ይጠቅማል ነዉ።በዚሕ ሒደት የኩልነት መርሕ ሥፍራ የለዉም።ለበረራ ደሕንነት የመንገደኛዉ የዘር ግንድ፥ሐይማኖት፥እድሜ፥የኑሮ ሁኔታ ወሳኝ ሚና አላቸዉ።እስራኤላዊዉ የአሸባሪነት ጉዳይ አዋቂ አርየል ሜራሪ የዚሕን ሐሳብ ያብራራሉ። የመንገደኛዉ «የዘር ታሪክን ማጠናቀር» ይላሉ ሜራሪ ለበረራ ደሕንነት «ዉጤታማና ምትክ የለሽ ነዉ።» እስራኤላዊዉ የአሸባሪነት ጉዳይ አዋቂ ከሆሎኮስት ጭፍጨፋ ከዳነ ይልቅ አንድ ሙስሊም ወጣት አደገኛ ነዉ።

ያም ሆኖ እስራኤል ዉስጥ የአካል መመርመሪያ መሳሪያ አለ።ግን አዉሮፕላን ጣቢያ አይደለም።ከጋዛ ወደ እስራኤል መግባት የፈለገ ሰዉ በመስተዋት በተከበበ ቃሪጮ መሐል ማለፍ አለበት። በመቆጣጠሪያዉ መስኮት (ስክሪን) የሚታየዉ የመስተዋቱ ሚስጥር እንዲሆን ተስፋ ማድረግ ነዉ።

Sabastian Engelbrecht

Negash Mohammed

Audios and videos on the topic