የቆጵሮስ የገንዘብ ቀውስና መዘዙ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 20.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የቆጵሮስ የገንዘብ ቀውስና መዘዙ

የአውሮፓ ህብረት ለቆጵሮስ በሚሰጠው ብድር ላይ የሚነጋገረው ኒቆስያ አማራጭ የመፍትሄ እቅዶችን ካቀረበች ብቻ መሆኑን አስታወ4ል ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የህብረቱ ባለሥልጣን ኒቆስያ ተጨባጭ አማራጮችን እስካላቀረበችለት ድረስ ህብረቱ በጉዳዩ ላይ ዳግም እንደማይመክር ተናግረዋል ።

የአውሮፓ ህብረት ለቆጵሮስ ያወጣውን የብድርና የገንዘብ እርዳታ ስምምነት የሃገሪቱ ፓርላማ ውድቅ ካደረገው በኋላ ፣ ህብረቱ በጉዳዩ ላይ የሚነጋገረው ኒቆስያ አማራጭ የመፍትሄ እቅዶችን ካቀረበች ብቻ መሆኑን አስታወቀ ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የህብረቱ ባለሥልጣን ኒቆስያ ተጨባጭ አማራጮችን እስካላቀረበችለት ድረስ ህብረቱ በጉዳዩ ላይ ዳግም እንደማይመክር ተናግረዋል ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የአውሮፓ ህብረት ፣ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ለቆጵሮስ ከቅድመ ግዴታ ጋር 10 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር ተስማምተው ነበር ። በቅድመ ግዴታው መሠረት የኒቆስያ መንግሥት ከሃገር ውስጥ 5.8 ቢሊዮን ዩሮ እንዲያሰባስብ ተጠይቋል ። ስለ ቆጵሮስ የገንዘብ ቀውስና መዘዞቹ የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን በስልክ አነጋግረናል ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic