የቀድሞው ሰላይ ስኖውደንና እጣ ፈንታው | ዓለም | DW | 24.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቀድሞው ሰላይ ስኖውደንና እጣ ፈንታው

ላለፉት 10 ቀናት ሆንኮንግ ከቆየ በኋላ ትናንት ሩስያ መግባቱ የተነገረው ስኖውደን ምናልባትም ዛሬ ከሩስያ ወደ ኤኳዶር ሳያቀና አልቀርም የሚሉ ዘገባዎችም ወጥተዋል። የኤኳዶር መንግሥት አሜሪካን ስኖውደን ተላልፎ እንዲሰጣት ያቀረበችውን ጥያቄ እያጠና መሆኑን አመልክቷል።

የአሜሪካንን የስለላ መርሃ ግብር ያጋለጠው የቀድሞ አንድ የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖውደን ስለሚገኝበት ሁኔታ የተለያዩ ዘገባዎች እየወጡ ነው። ላለፉት 10 ቀናት ሆንኮንግ ከቆየ በኋላ ትናንት ሩስያ መግባቱ የተነገረው ስኖውደን ምናልባትም ዛሬ ከሩስያ ወደ ኤኳዶር ሳያቀና አልቀርም የሚሉ ዘገባዎችም ወጥተዋል። የኤኳዶር መንግሥት አሜሪካን ስኖውደን ተላልፎ እንዲሰጣት ያቀረበችውን ጥያቄ እያጠና መሆኑን አመልክቷል። ሩስያም ስኖውደን ተላልፎ እንዲሰጣት ከአሜሪካን የቀረበላትን ጥያቄ በማጥናት ላይ መሆኗን ብታሳውቅም ስኖውደን የሩስያን ድንበር ያቋረጠው አሳውቆ ስላልሆነ ሩስያ ግለሰቡን የመያዝም ሆነ የማባረር መብት እንደማይኖራት ኢንተርፋክስ የተባለው ዜና አገልግሎት አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ የዋሽንግተን ዲሲውን ዘጋቢያችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic