የሶርያ ስደተኞች ይዞታ | ዓለም | DW | 09.02.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሶርያ ስደተኞች ይዞታ

የሶርያ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ተቃዉሞ በቀጠለባት የሆምስ ከተማ ጥቃታቸውን ማጠናከራቸውና ሩስያና ቻይናም በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የቀረበውን የሶርያ ረቂቅ ውሳኔን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸው ተጠቅመው ያገቱበት ድርጊት ከያቅጣጫው ብዙ ወቀሳ ተፈራርቆበታል።

የሶርያ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ተቃዉሞ በቀጠለባት የሆምስ ከተማ ጥቃታቸውን ማጠናከራቸውና ሩስያና ቻይናም በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የቀረበውን የሶርያ ረቂቅ ውሳኔን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸው ተጠቅመው ያገቱበት ድርጊት ከያቅጣጫው ብዙ ወቀሳ ተፈራርቆበታል።

የተመድ በሶርያ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ አንጻር ርምጃ እንደሚወስድና ካለፈው መጋቢትም ወር ወዲህ የስድስት ሺህ ሰዎችን ሕይወት ያጠፋውን የኃይል ተግባር እንደሚያበቃ ብዙዎች ተስፋ አድርገው ነበር። ፕሬዚደንት አሳድ በሀገራቸው የቀጠለውን ደም መፋሰስ እንዲያበቁ ዐረባውያት ሀገሮች ያቀረቡላቸውን ሀሳብ ባለመቀበላቸው የባህረ ሠላጤው ሀገሮች አምባሳደሮቻቸውን ከሶርያ አስወጥተዋል። ብዙ ሶርያውያንም የመንግሥቱን ፀጥታ ኃይላት ጥቃት ሸሽተው ወደ ጎረቤት ቱርክ ተሰደዋል።
የፕሬዚደንት አሳድ ፀጥታ ኃይላት ባለፈው ሰኔ ወር በሰሜናዊ ሶርያ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በደመሰሰበት ጊዜ ወደ ሰባት ሺህ የሚጠጉ ሶርያውያን ወደ ጎረቤት ቱርክ በመሰደድ በዚያ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች መኖር ጀምረዋል። ይሁንና፡ የዶይቸ ቬለ ዘጋቢ ማሪነ ኦሊቬዚ ያነጋገረቻቸው እና ቀሪው ዓለም ሶርያን ችላ እንዳለ የተሰማቸው ብዙዎቹ ስደተኞች አሁን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ተመልሰው እንደሚታገሉ ገልጸውላታል።


የሆምስ ከተማ በተኩስ መደብደቧ፡ ሩስያና ቻይናም የሶርያ የኃይል ርምጃ እንዲያወግዝና የጦር መሣሪያ ማዕቀብ እንዲያሳርፍ ሆኖ የተዘጋጀውን እና የዐረብ ሊግ የደገፈውን ረቂቅ ውሳኔ በሩስያና በቻይና እምቢታ መክሸፉ በቦርቺን መጠለያ ጣቢያ ያሉትን ስደተኞች እያነጋገረ ነው። በመጠለያው ጣቢያ ብቸኛው የሆምስ ተወላጅ የሆኑት ዋሲም ሳባግ ትውልድ ከተማቸው ባለፈው ዓርብ መደብደቧን ወዲያውኑ ነበር የሰሙት።
« ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ነበረ። ዜና እየተከታተልን እያለን ከተማይቱ መደብደቧን ሰማን። ያኔ ሁሉም በጣቢያው ያሉት ሌሎቹ ሁሉ ሆምስ ውስጥ ምን እየተፈጸመ መሆኑን በዓይናቸው እንዲያዩ እየዞርን ቀሰቀስናቸው። ታድያ አንዳንዶቹ ወዲያውኑ በዚያች ቅፅበት የሆነ ነገር ማድረግ ነበር የፈለጉት። »


ዋሲም አክለው እንዳስረዱት፡ አንዳንዶች ወደ ሆምስ የሚላክ ደም ለደም ባንክ ለመስጠትም ፍላጎት ነበራቸው። ግን፡ ሀሳቡ ዕውን ሊሆን የማይችል መሆኑን አልዘነጉትም፤ ምክንያቱም ደሙን በድብቅ ወደ ሆምስ ማስገባት እጅግ አዳጋች ነውና። ይህ እንደማይሆን የተገነዘቡ አንዳንዶች አምስት ኪሎሜትር ገደማ ርቆ ወደሚገኝና የነፃ ሶርያ ጦር መኮንኖች ወዳሉበት አንድ ሌላ መጠለያ ጣቢያ በእግራቸው በመጓዝ መፍትሔ ለማፈላለግ ሞክረዋል። ግን ድጋፍ እንዳላገኙ የገለጹላቸው የጦር መኮንኖች ምንም መልስ ሊሰጡዋቸው አልቻሉም።
ሩስያና ቻይና በፀጥታ ጥበቃ ምክር ረቂቁን ውሳኔ ማገዳቸው የተመድ ዲፕሎማቶችን እንዳስቆጣ ሁሉ በቦርቺ መጠለያ ጣቢያ ያሉትን ሶርያውያን ስደተኞችም እጅግ ማስደንገጡን ጠበቃው ጋዝዋን ሀጅ ኢሳ ገልጸዋል።
« በፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የሆነው ጉዳይ ለስብዓዊ ፍጡር ባጠቃላይ አሳፋሪ ነው። ምክንያቱም፡ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ተግባር የዓለም ሕዝብን ደህንነትን መከላከል ነውና። ይሁንና፡ ርምጃ ባለመውሰዱ ግድያውን ደግፎዋል። እስካሁን በሶርያ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል። በዚያ የቀጠለውን ግድያ ማንም ሊያስቆመው አልቻለም። የሚያሳፍር ነው። »


በዚህም የተነሳ በቱርክ ድንበር የሚገኙት ሶርያውያኑ ስደተኞች እጃቸውን አጣምረው መቀመጥ እንደማይፈልጉ እየገለጹ ነው። አንዳንዶች በድንበሩ አካባቢ በሚገኘው ኬላ የቁጭታ አድማ ለማደራጀት፡ ሌኦች ደግሞ በፌስቡክ ገንዘብ ለማሰባሰብ እየሞከሩ ነው። ሌሎች ደግሞ በድብቅ ሀገራቸው ለመግባት ቢፈልጉም፡ የብረቱን ትግል በመቀላቀሉና ባለመቀላቀሉ መካከል መወሰን አቅቶዋቸዋል። ይሁንና፡ ብዙዎቹ እንደሚሉት፡ ሰላማዊው ትግል ውጤታማ የሚሆነው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለመርዳት ሲፈልግ ብቻ ነው።

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች