የሶርያው መሪ የሩሲያ እና የኢራንን ድጋፍ አወደሱ | ዓለም | DW | 04.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሶርያው መሪ የሩሲያ እና የኢራንን ድጋፍ አወደሱ

የሶሪያው ፕሬዚዳንት በሽር አል-አሣድ የሩስያ፣ የኢራን፣ የኢራቅ እና የሶሪያ ጥምር ኃይል በሶሪያ ድልን ባይጎናፀፉ ኖሮ ሀገሪቱ ከመውደም አትተርፍም ነበር ሲሉ ለኢራን ቴሌቪዥን ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት በሽር አል-አሣድ በኢራን የፋርስ ቋንቋ ትርጁማን እየተተረጎመ በአረቢኛ ባደረጉት ንግግር፦ ጥምሩ ኃይል ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል እምነታቸው ጠንካራ እንደነበር፣ የተገኘው ድልም እጅግ አመርቂ እንደሆነ ገልጠዋል። ጥምር ኃይሉ አሸባሪዎችን ለመዋጋት ባደረገው የጋር ትግል በስኬት ሊደመደም የቀረው ጥቂት እንደነበር፤ ሆኖም ይህን ጥረት የሚያስተጓጉሉ ተግባራት የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ላይ ይኼ ነው የማይባል ጥፋት ሊያስከትል እንደሚችል ፕሬዚዳንት በሽር አስጠንቅቀዋል። በሶሪያ እና በኢራቅ የሚገኘው ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» እያለ የሚጠራው ቡድን ላይ ምንም እንኳን ዩናይትድ ስቴትስ እና ተባባሪዎቿ ለዓመት የተራዘመ የአየር ጥቃት ቢያከናውኑም ግጭቱና ቀውሱ ይበልጥ እንደተባባሰ፤ በአንፃሩ አራቱ ሃገራት «ከፊል ስኬት» መቀዳጀታቸውን ፕሬዚዳንት በሽር አል አሣድ ጠቅሰዋል። ሶሪያ እና ተባባሪዎቿ ሊሳካላቸው ይገባል «አለበለዚያ በአካባቢው ሃገራት በአጠቃላይ ጥፋት ይከሰታል» ሲሉ ፕሬዚዳንቱ በአጭር መልእክት ማሠራጪያ ትዊተር ማኅበራዊ መገናኛ ገፃቸው አስጠንቅቀዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ