የስድተኞች መልስ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 04.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የስድተኞች መልስ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት፣ በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ (IOM) ውጊያ ካመሰቃቀላት የመን 485 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ማስወጣቱን አስታወቀ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ አቶ አለማየሁ ሰይፈስላሤ እንደተናገሩት፣ እነዚህ ባለፈው ወር ያስወጣቸው ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:23
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:23 ደቂቃ

የኢትዮጵያ ስድተኞች

በሳውዲ መራሹ የሳውዲ ዐረቢያ ጦር በሚረዳው የ የመን መንግሥት ጦር እና በአንፃሩ በሚዋጉት የሁቲ ዓማፅያን መካከል የቀጠለው ውጊያ በዚችው ሀገር የሚገኙትን ስደተኞችን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ጥሎዋቸዋል። በዚህም የተነሳ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ስደተኞቹን ከየመን ለማስወጣት ጥረት ጀምሮዋል።

በምህፃሩ «አይ ኦ ኤም» ተብሎ የሚጠራው ድርጅት፣ የሚጠራዉ ካለፈው መጋቢት ወር እሳላፈው ዓርብ ድረስ በየመን ጦርነት መሃል ተጠምደው ሲንገላቱ የነበሩ 1, 220 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገር መመለሱን ቃል አቀባይ አቶ አለማየሁ ሰይፈስላሤ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

እንደ አቶ አለማይሁ ገለፃ በኢትዮጲያ፣ በጂቡቲ እና በየመን የሚገኙት የ«አይ ኦ ኤም» መስሪያ ቤቶች በመተባበር ነው ስደተኞቹን የመመለሱን ስራ የሚያከናውኑት። ወደ ኢትዮጲያ ለመመለስ ማመለከቻ የሚያቀርብ ስደተኛ ተቋሙ የሚጠይቃቸውን የተወሰኑ መስፈርት ማሟላትም እንዳለባቸው አቶ ሰይፈስላሤ አስረድተዋል።


ስራ ፍለጋ እና የተሻለ ሕይወት ለመምራት ከኢትዮጵያ ወደ የመን ቀይ ባህርን አቋርጠው የሚሰደዱ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ ደላላዎች እጅ ብዙ ስቃይ እንደሚደርስባቸው እና ካሳ መክፈል እንደሚጠየቁ የ«አይ ኦ ኤም» ቃል አቀባይ አቶ አለማየሁም ገልጸዋል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic