የሳዴክ የመሪዎች ጉባዔ ፍጻሜ | ኤኮኖሚ | DW | 18.08.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የሳዴክ የመሪዎች ጉባዔ ፍጻሜ

አስራ አራቱ የደቡባዊ አፍሪቃ መንግስታት የልማት ድርጅት፡ በምህጻሩ ሳዴክ አባል ሀገሮች ርዕሳነ ቤር እና መራህያነ መንግስት በናሚቢያ መዲና ዊንድሁክ ያካሄዱትን የሁለት ቀናት ጉባዔ ትናንት ማምሻቸውን አጠናቀቁ።

default

የሳዴክን ዓቢይ ጉባዔ ያስተናገዱት የናሚብያ ፕሬዚደንት ሂፊኬፑንየ ፖሀምባ


መሪዎቹ በዚሁ ጉባዔ ላይ የድርጅታቸውን ሰላሳኛ የምስረታ ዓመትንም አክብረዋል። ጉባዔው በአስራ አራቱ የሳዴክ አባል ሀገሮች መካከል የኤኮኖሚውን ትብብር የማሳደግ ዓላማ ይዞ የተነሳ ነበር። በአባል ሀገራት ማዳጋስካር የቀጠለው የፖለቲካ ውዝግብ እና በዚምባብዌ የተደረሰው የስልጣን መጋራት ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያልሆነበት ድርጊትም ጉባዔው ትኩረት ያሳረፈባቸው ሌሎች ጉዳዮች ነበሩ።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic