የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ምሕረት
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 28 2009ማስታወቂያ
የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸዉ ከታሰሩ ኢትዮጵያዉን መካከል ለ375ቱ ምሕረት አድርገዋል።ንጉሱ ምሕረቱን ያደረጉት ከኢትዮጵያዉ ፕሬዝደንት ከሙላቱ ተሾመ በቀረበላቸዉ ጥያቄ መሠረት ነዉ።እስረኞቹ የሚፈቱበት ጊዜ፤ የነበሩበት ሁኔታና ወደ ሐገራቸዉ የሚጓዙበት መንገድ ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም።የሪያዱ ወኪላችን ስለሺ ሽብሩ እንደሚለዉ ግን ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያዉን እስረኞች ምሕረት ስታደርግ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።ሥለሺሕ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ስለሺ ሽብሩ
ነጋሽ መሐመድ