የሳምንቱ የስፖርት ዝግጅት | ስፖርት | DW | 23.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የሳምንቱ የስፖርት ዝግጅት

በየሳምንቱ በዚህ ሰዓት የሚቀርበው ዓለም አቀፍ የስፖርት መሰናዶአችን እንሆ።በዝግጅቱ ከተካተቱት መካከል እግር ኳስ፤ አትሌቲክስና የአውቶሞቢል እሽቅድድም ይገኙበታል።

ከአፍሪቃ ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ፤ ከ 10 ሩ የሚያልፉት 5 ቡድኖች የሚታወቁት በመጪው ጥቅምትና ኀዳር በሚካሄዱ የደርሶ መልስ ግጥሚያዎች ነው። ኢትዮጵያ የደረሳት ዕጣ ፤ ከናይጀሪያ ጋር ሲሆን፤ ከወዲሁ፣ ከሁለቱም ወገን ዝግጅትን በተመለከተ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ። የኢትዮጵያ ቡድን ፤ የጨዋታ ጥበብ አያንሰውም ፤ ያም ሆኖ የአቅም ጥንካሬ ፣ ስልት የመቀያየር ብልሃትና «ዲሲፕሊን» ግን እንደሚያሻው ፣ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ፤ በአፍሪቃ ዋንጫ ፤ ቡድኑ ከናይጀሪያ ጋር ያካሄደውን ጨዋታ የሚያስታውሱ አንዳንድ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ይህን፤ አሠልጣኝ አቶ ሰውነት አሳምረው ስለሚያውቁት ፤ ቡድኑን በሚገባ እንደሚያዘጋጁት ይታሰባል። አሁን በቀጥታ ወደ ሳምንታዊው የአስፖርት ዘገባ እንሸጋገር።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic