የሳምንቱ ባህል ነክ ዜናዎች በአዉሮጻ / 4ኛዉ አዲስ የፊልም ፊስቲቫል | ባህል | DW | 08.04.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሳምንቱ ባህል ነክ ዜናዎች በአዉሮጻ / 4ኛዉ አዲስ የፊልም ፊስቲቫል

በአዲስ አበባ ከተማችን ለ 4ኛ ግዜ ስለተካሄደዉ አዲስ አለም አቀፉ የፊልም ፊስቲቫል ተጠናቆአል። ኢኒሼቲቭ አፍሪቃ በመባል በሚታወቀዉ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የተጀመረዉ እና ዘንድሮ አራተኛ አለማቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ላይ የደረሰዉ

default

አዲስ የፊልም መድረክ ከመጋቢት17 እስከ መጋቢት 26 አገራችን አቆጣተር በ1970 ዎቹ በሎሪት ጸጋዪ ገብረ መድህን ተደርሶ በአቶ አባተ መኩርያ የተሰራዉ ታዋቂዉ የመቅደላ ስንብት ትያትር ላይ የቴድሮስን ባህሪ የሚጫወተዉ የኪነ-ጥበብ ሰዉ የዛሪዉ የባህል መድረክ እንግዳችን ነዉ። በአዲስ አበባ ከተማችን ለ 4ኛ ግዜ ስለተካሄደዉ አዲስ አለም አቀፉ የፊልም ፊስቲቫል ተጠናቆአል። ኢኒሼቲቭ አፍሪቃ በመባል በሚታወቀዉ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የተጀመረዉ እና ዘንድሮ አራተኛ አለማቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ላይ የደረሰዉ አዲስ የፊልም መድረክ ከመጋቢት17 እስከ መጋቢት 26 በአገር ዉስጥ እና በተለይ በተለያዩ አፍሪቃ አገሮች የተሰሩ ዘጋቢ ማለት ዶኩመንተሪ ፊልሞች ላይ አዉደ ጥናት አድርጎ አሸናፊም መርጦ ፊስቲቫሉ መጠናቀቁ ተገልጾአል። በኢትዮጽያ የፊልም ሰራተኞች ማህበር ፕሪዝዳንት ሃይማኖት አለሙ፣ ስኢትዮጽያ የፊልም ስራ ሁኔታ እና ስለፊስቲቫሉ ያጫዉቱናል። ሌላዉ ሰሞኑን በጀርመን የተለያዩ የባህል ደረ-ገጾች ላይ ከሰፈሩ አብይ ርእሶች መካከል

ግሪክ ላይ የደረሰዉ የኢኮነሚ ቀዉስ በተለይ በአዉሮጻ ዉስጥ ለሳምንታት በብዙ ዘርፎች ሲያነጋግር የሰነበተ ጉዳይ ነዉ። በግሪክ የደረሰዉን የኢኮነሚ ችግር ለመቋቋም መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ከሚመድበዉ በጀት አስር በመቶ ለመቀነስ ዉሳኔ ላይ ደርሶአል። ጀርመናዉያን የኢኮነሚ አዋቂዎችን ጠቅሶ የዶቸ-ቬለዉ የጀርመንኛ የባህል ድረ-ገጽ እንደዘገበዉ በግሪክ ምንም አይነት ከባድ ኢንዱስትሪ አለመኖሩ ግልጽ መሆኑን በመጥቀስ፣ በዚህም ይላል በዝርዝሩ ግሪክ ታሪክዋን እና ባህሏን በመንተራስ በቱሪዝም፣ በትያትር በቤተ መዘክር ልዪ እና ዋንኛ ገቢን የምታገኝ ጥንታዊ ታሪክ ያላት አገር መህዋን ይጠቅሳል። የደረሰዉን የኢኮነሚ ችግር ለመቋቋም የስልጣኔ በር በመሆንዋ የምትታወቀዉ ግሪክ በባህል እና በቱሪዝም ዘርፎች መንግስት የሚመድበዉን በጀት እንደተጠቀሰዉ አስር በመቶ ቅናሽ ላያደርግ እንደሚችል ይተነትናል። ምክንያቱም እንደ ግሪክ መንግስት እቅድ ባህልን የተንተራሰ ማንኛዉም የአገሪቷ ሃብት ገንዘብ እና ቱሪስትን ማግኛ ዋንኛ መሰረት ናቸዉ። በዚህም በአገሪቷ ቅርጽ እና ባህል በጥብቅ ይጠበቃል። ለዚህም ከመንግስት በትክክለኛ መንገድ ለቅርስ ለባህል እና ለታሪክ በጀት ይፈሳል። መንግስት የአገሪቷን የባህል ቅርስች በመጠበቅ ቱሪዝምን ለማስፋፋት ልዩ ጥናት እና አዳዲስ ሃሳብን በማፍለቅ በአገሪቷ የደረሰዉን ችግር ባፋጣኝ ለማቃለል መሰረት ሊሆን ይችላል ሲል በግሪክ ለደረሰዉ የኢኮነሚ ችግር በባህሉ ዘርፍ ያለዉን የመፍቻ ሃሳብ ሰጥቶል።

Stasi-Akten über Kohl werden herausgegeben

የቀድሞ የጀርመን መራሄ መንግስት ሄልሞት ኮል


የቀድሞ የጀርመን መራሄ መንግስት ሄልሞት ኮል ባለፈዉ ቅዳሜ 80ኛ አመታቸዉን ማክበራቸዉ ነዉ። ጀርመናዉያን በቋንቋቸዉ Der Kanzler der Einheit የአንድ መሆናችን መለያ ቻንስለራችን የሚልዋቸዉ ሄልሙት ኮል እ.አ 1982 እስከ 1998 አ.ም የጀርመን መራሄ መንግስት በመሆን 16 አመት፣ የክርስትያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ በመሆን 25 አመት ማገልገላቸዉ ተገልጾላቸዋል። ሄልሙት ኮል ይህንን ሁሉ አመት ስልጣን ሳያስረክቡ በመሪነት ደረጃ መቆየታቸዉ ለተተኪ ስልጣን ባለማስተላለፋቸዉ፣ አገሪቱን ምናልባት በፍጥነት እንዳትራመድ አድርገዋታል የሚል ወቀሳ አልፎ አልፎ ከፖለቲከኞች ሲሰነዘር ይሰማል። ምክንያም አንድ የአገር መሪ በሰለጠነዉ የምዕራባዉያኑ አገራት ከአስር አመት በበለጠ ስልጣን ላይ የመቆየት ባህል ባለመኖሩ። ይሁንና በሌላ በኩል ሄልሙት ኮል የቀዝቃዛዉ ጦርነት ማብቅያ የጀርመን ዉህደት መሰረት እንዲሁም የአዉሮጻ አገሮች አንድነት መሰረት ተጠቃሽ ቁንጮ እንደሆኑ ጀርመናዉያን በኩራት ይገልጹላቸዋል። ሄልሙት ኮልም ቢሆኑ ለልደታቸዉ አከባበር ዋንጫን አንስተዉ ምስጋናን ሲያቀርቡ የጀርመን ዉህደት አሁንም የሚያስደስታቸዉ መሆኑን በኩራት ገልጸዋል። እርጅና ተጫጭኖአቸዉ ትንሽም የጤና ችግር ስላጋጠናቸዉ በተሽከርካሪ ወንበር የሚንቀሳቀሱት ሄልሞት ኮል በራይን ላይድ ፓላቲኔት ግዛት በኦገርስ ሃይም ከተማ ከሁለተኛ ባለቤታቸዉ ጋር ስድሳ ከሚሆኑ የቅርብ ጓደኛ እና ዘመዶቻቸዉ ጋር በዝግ ልደታቸዉን ማክበራቸዉ ተገልጾአል። ይሁንና በራይን ላይድ ፓላቲኔት ዋና ከተማ በሆነችዉ በሉድቪግስ ሃፈን በመጭዉ ሚያዝያ 27 ጥሪ ከተደረገላቸዉ የዉጭና የአገር ዉስጥ እንግዶች በከፍተኛ ስነ-ስርአት የልደት በአላቸዉ እንደሚከበርላቸዉ ተገልጾአል።

የጀርመንን የሙዚቃ አፍቃሪ ልብ አሁንም በማጠያየቅ ላይ ያለዉ የአለም የሞፕ የሙዚቃ ንጉስ የማይክል ጃክሰን አሟሟት ጉዳይ በያዝነዉ ሳምንት የጀርመናዉያኑ የባህል መድረክ ድረ-ገጾች የዘገቡበት ጉዳይ ነዉ። ማይክል ጃክሰንን ከመጠን ያለፈ እና ሊሰጠዉ የማይገባ መድሃኒትን ሰጥተህ ገድለሃል የተባለዉ የማይክል ጃክሰን የግል ሃኪም በሳምንቱ መጀመርያ በዩናይትድ ስቴትስ ሎስ አንጀለስ ከተማ በፍርድ ሂደት ጉዳዩ ሲታይ ዉሎአል። በፍርዱ ሂደት ከፍርድ ቤቱ አካባቢ ቆመዉ ይጠባበቁ የነበሩ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ አፍቃሪዎቹ We are the World የተሰኘዉን የማይክልን እዉቅ ሙዚቃ በማዜም የፍርዱን ሂደት ሲጠባበቁ መቆየታቸዉ ተገልጾአል። የማይክል ጃክሰን የግል ሃኪም ማይክልን በህይወቱ የመጨረሻ ሰአታት ያየዉ ሰዉ ነዉ የሚል እምነት አለ። የማይክል እናት አባት ወንድም እህቶች ፍርዱን ለመከታተል በፍርድ ቤት ተገኝተዉ ነበር። የማይክል ጃክሰን የግል ሃኪም ጠበቃ እንደገለጸዉ ተከሳሽ ሃኪም ማይክልን የሚገባዉን ክትትል አድርጎለት እንደተለየዉ እና እራሱ ማይክል ፕሮፖፎል የተሰኘዉን መድሃኒት ከመጠን ባለፈ ሁኔታ በመዉሰዱ ህይወቱ አልፎአል ሲሉ መግለጻቸዉ እና መከራከራቸዉ ተገልጾአል። በዚህም ጉዳይ ለመጭዉ ሰኔ ሰባት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተወስኖ የለቱ የፍርድ ሂደት መጠናቀቁ ተገልጾአል።

EM 2004 - griechischer Fußball-Jubel in Köln

እግር ኳስ ጨዋታን ባህሉ ላደረገዉ የጀርመን ህዝብ ትናንት ምሽት በጀርመኑ የባየር ሙኒክ የእግር ኳስ ቡድን እና በእንግሊዙ የማንቸስተር ዩናይትድ የአዉሮጻ ክለቦች ሻንፒዮና ሊግ የአራታኛ ማጣሪ ግጥምያ ከፋሲካ ድግስ እና እረፍት በኻላ በተለይ ለጀርመናዉያኑ የእግር ኻስ አፍቃሪዎች ጥሩ እና የተሳካ የመዝናኛ ምሽት እንደሆነላቸዉ የባህሉ ድረ-ገጽ ዘግቦታ። በእንግሊዝ ለተካሄደዉ ግጥምያ በጀርመናዉያኑ የሰአት አቆጣጠር ለምሽቱ ሁለት ሰአት ግድም የጀመረዉ ይኸዉ ግጥምያ በጀርመን ከተሞች ያሉ ሆቴሎችና እና የቢራ መጠጫ መድረኮች ዳግም ሰፋ ያለዉን የቴሌቭዥን መስኮታቸዉን ወጣ አድርገዉ ህዝብን እንዲያስተናግዱ ሆንዋል። በርግጥ ጨዋታዉ ከመጀመሩ በጀርመን ያለዉ የአየር ጸባይ ለቢራ ለመጠጣት እንዲሁም የተለበሰ ጃኬትም ወለቅ ለማድረግ ቢገፋፋም ጀርመናዉያኑ የእግር ኻስ አፍቃሪዎች የግጥምያዉ አጀማመር በማንቸስተሩ ቡድን ልዪ የጨዋታ ጥንካሪ የባየር ሙኒኩ ጨዋታ ተሸፍኖ ቆይቶ ለባየር ምንም አይነት እድል ያልታየበት ሆኖ ቆይቶ ነበር። ሁለተኛዉ አጋማሽ የጨዋታ ሰአት የባየር ሚኒክ የእግር ካስ ቡድን ባገኘዉ የግብ እድል ከዘንድሮዉ አራቱ ምርጥ የአዉሮጻ የእግር ኻስ ቡድን በመደብ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፉ፣ የጀርመን የባህል ድረ-ገጾችም ሆነ ከፋሲካ በአል እረፍት ማግስት ስራ ለጀመሩት ጀርመናዉያን በዉጤቱ ዳግም እረፍትን አስገኝቶላቸዉ አምሽቶአል።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ