የሰማያዊ ፓርቲ ዉዝግብ | ኢትዮጵያ | DW | 30.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ ዉዝግብ

የሰማያዊ ፓርቲ የሥነስርዓት ኮሚቴ በፓርቲዉ ሊቀመንበር እና በሌሎች ሦስት የአመራር አባላት ላይ ያስተላለፈዉ የእገዳና ማባረር ዉሳኔ የፓርቲዉ የኦዲት ኮሚሽን ተፈፃሚ እንዳይሆን አገደ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:10

ሰማያዊ ፓርቲ

የፓርቲዉ የኦዲት ኮሚሽን ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ ዉሳኔዉ ተግባራዊ እንዳይሆን በመወሰን በቅርቡ በጉዳዩ ላይ ጥልቀት ያለዉ ምርመራ አካሂዶ የመጨረሻ ዉሳኔ እንደሚያስተላልፍም ገልጿል። የፓርቲዉ የሥነስርዓት ኮሚቴ በበኩሉ የኮሚሽኑ ዉሳኔ እንዳልደረሰዉ እና በሥራዉ ላይ ግን ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተናግሯል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic