የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታና መግለጫው | ኢትዮጵያ | DW | 02.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ አቤቱታና መግለጫው

ግንቦት 25 2005 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ባካሄደው ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ለመንግሥት ያቀረባቸው ጥያቄዎች መልስ ካላገኙ በድጋሚ ሌላ ተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ማሳወቁ ይታወሳል።

ይህም ሰልፍ ለነሐሴ 26 ነበር የታቀደው። ነገር ግን ፓርቲው ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ እንዳለ ተነግሮት ትናንት በተካሄደው ሰልፍ ሆን ተብሎ መንግስት ፓርቲው የጠራውን ሰልፍ ማክሸፉን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሮን ሰይፉ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። ሰልፉ አለመካሄዱ ብቻ ሳይሆን ምርጫው ሊካሄድ በታቀደበት ዋዜማም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጨምሮ የፓርቲው ከፈተኛ አመራሮች በፖሊስ መታገታቸውን አቶ አሮን ገልፀዋል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፁት ሰማያዊ ፓርቲ ያቀደዉ ሰልፍ መጨናገፉን ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክቶ በድጋሚ ለፊታችን ቅዳሜ ሌላ ህዝባዊ ሰልፍ እንሚጠራ አስታዉቋል። ይህንኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ተከታትሎ ቀጣዩን ልኮልናል። ከቀጣዮቹ የድምፅ ዘገባዎች ያገኙታል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic