የምንያማር ቀውስ እና የኡንግ ሳን ሱ ቺ ምላሽ | ዓለም | DW | 19.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የምንያማር ቀውስ እና የኡንግ ሳን ሱ ቺ ምላሽ

የምናይማሯ መሪ ኡንግ ሳን ሱ ቺ በስተመጨረሻ በሮሒንጃያ ሙስሊሞች ላይ ሥለሚፈፀመዉ ግፍ  ዝምታቸውን ሰበሩ። የኖቤል ሽልማት ባለቤቷ ሱ ቺ የሐገራቸዉ ጦር የሚያደርሰዉን በደል እንዲያወግዙ የጠበቁ ግን አዝነውባቸዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:26

የኡንግ ሳን ሱ ቺ ምላሽ

ሱ ቺ ዛሬ  ባደረጉት ንግግር የምያንያማርን ቀውስ ለማስወገድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያግዛቸው ይጠይቁ እናጂ የግድያ፤አስገድዶ መድፈር እና መንደር የማቃጠል ዘመቻ ያካሒዳል ተብሎ የሚወቀሰውን የአገራቸውን ጦር መተቸት አልሆነላቸውም። "ሁሉንም የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ኹከት እናወግዛለን" ያሉት ሱ ኪ በግጭቱ መከራ ለዘነበባቸው ሰዎች እናዝናለን ሲሉ አክለዋል። ሱ ቺ ዓለም በጉጉት የሚጠብቀውን ንግግር ሲያደርጉ ግን ከ400,000 በላይ የሮሒንጃያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከቀያቸው ተፈናቅለው ስደት ላይ ናቸው። የቡድሐ እምነት ተከታዮች የሚበዙበት የምንያማር መንግሥት በአናሳዎቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈፅመውን ተግባር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ማጽዳት ሲል መኮነኑ አይዘነጋም። 

ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic