የምርጥ ድረ-ገፅ ዓለማቀፍ ሽልማት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 05.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የምርጥ ድረ-ገፅ ዓለማቀፍ ሽልማት

ዶቼ ቬለ በየዓመቱ «ምርጥ የድረ-ገፅ አምድ» በመባል የሚታወቀዉን ሽልማት በዓለማችን ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረጋቸዉ የሚታወቁ ድረ-ገፆችን በማወዳደር ይሸልማል። በዓለም ዙርያ በድረ-ገጽ ላይ የስለላ ተግባር እጅግ እየተጣነከረ በመምጣቱ በርካታ ተጠቃሚዎች የግል ምስጢራዊ ሰነዳችን በሌሎች እጅ ይወድቃል በሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል።

ዶቼ ቬለ ዘንድሮ ለአስረኛ ግዜ በኢንተርኔት የመረጃ ትስስር ዓለም አመርቂ እንቅስቃሴን ያደረገ ድረ-ገፅ እና አምደኛን በማወዳደር፤ ዘ-ቦብስ የተሰኘዉን ሽልማት ለማበርከት በዝግጅት ላይ ነዉ። የዶቼ ቬለዉ « ዘ ቦብስ» ዓለማቀፍ ሽልማት፤ አምደኞች ለዉድድር የሚያቀርቡትን የድረ- ገፅም ሆነ የአምድ ፕሮጄ ፅንሰ -ሃሳብ እስከ መጋቢት አምስት ያላቸዉን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።


ለዓመቱ ምጥ ድረ-ገፅ ዶቼ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ ዘ-ቦንስ የተሰኘዉ ዓለማቀፍ ሽልማት ከጎርጎረሳዉያኑ 2004 ዓ,ም ጀምሮ ሃሳብን በነፃነት የሚገልፁ ግለሰቦችን ሚስጥር ለሚጠብቁ ድረ-ገፆችና አምደኞች እዉቅና ይሰጣል። ለምንገኝበት ለዚህ ለአዲሱ በመረጃ መረብ ለተሳሰረ ዓለም፤ ሃሳብን በነጻነት ለመግለፅ አገልግሎቱን የመጠቀም እድል ያላቸዉ ከፍተኛ ተጠቃሚ ናቸዉ ሲሉ፤ ፓምፖሎና፤ ስፔን፤ ናቫራ ዩንቨርስቲ ዉስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ ምሁርና « ዘ ቦብስ»የሽልማት ሰጭ ኮሚቴ ዉስጥ የቀድሞዉ ገምጋሚ ፕሮፊሰር ጆሴ ሉይስ ኦሪሆየላ ይገልፃሉ ። እንደ ኦሪሆየላ በአሁኑ ወቅት የድረ-ገፅ አምድንና ኢንተርኔትን መጠቀም የሚስችል ተንቀሳቃሽ ስልክ፤ በመገናኛ ብዙሃን መድረክ ከፍተኛ ለዉጥን አስገኝተዋል። በዚህ አኳያ በርካታ ሰዎች መረጃን ማሰረጫትና እራሳቸዉም መረጃን በማቀበሉ መሳተፍ ችለዋል። ከሁሉ በበለጠ ግን የግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃ መጠበቁ አስፈላጊ መሆኑን ኦሪሆየላ ያሰምሩበታል።
የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች፤ በድረ- ገፅ ሃሳባቸዉን በነጻነት መግለፃቸዉ፤ በሚኖሩባቸዉ የተለያዩ ሃገራት ሊደርስ የሚችለዉ አደጋም እንዲሁ የተለያየ ነዉ። ፍሪደም ሃዉስ የተሰኘዉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት፤ በየዓመቱ በሚያወጣዉ ዘገባ መሰረት፤ በጎርጎረሳዉያኑ 2013 ዓ,ም በዓለም ዙርያ በድረ- ገፅ ላይ ሃሳብን የመግለፅ ነጻነት ቀንሶአል። በጀርመን የጽረ-ገፅ ሃሳብን በነጻነት መግለፅ እና የድረ-መገናኛ ፤ ጉዳይ ተጠሪ ሃዉከ ጊሮቭ እንደሚሉት ፤ ምቾት የማይስጡ አጋላጭ ጋዜጠኞች እና አምደኞች፤ በአብዛኛዉ፤ ለችግር እና ለጥቃት የተጋለጡ በመሆናቸዉ፤ ዓለም ይህን ጉዳይ በንቃት ሊከታተለዉ ይገባል።
እንደ ቻይና እና ኢራን በመሳሰሉ ሃገሮች መንግስት ከአስር ዓመት ወዲህ፤ በድረ-ገፆች እና በኢንተርኔት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መቆጣጠር ጀምሮአል። ተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ አቀንቃኞች በበኩላቸዉ፤ ይህን የመንግስት ክትትል ለማምለጥ እና በሚያወጡት መረጃ በመንግስት ጥርስ ዉስጥ ላለመግባት፤ የኢንተርኔት ቴክኒካዊ ስልቶችንና መሸሸግያ ዘዴዎችን ማወቅ ግድ ሆኖባቸዋል።
እንደ ጊሮቭ በድረ-ገፅ ተጠቃሚ እና በድረ-ገፆች ላይ የሚወጡ መረጃዎችን ምርመራ(ሳንሱር) በሚያደርጉ መካከል ያለዉ ለዓመታት የዘለቀዉ የድመትና የአይጥ አይነት ስድጃ፤ ለምሳሌ በቻይና መንግስት የማይወደድ ድረ-ገፅን በተገኘዉ እና ባወጣዉ ወጭ ከፍሎ መዝጋት አሁንም የሚታይ ድርጊት ነዉ። አንድ የድንበር አያግዴዉ የዘጋቢዎች ድርጅት ባልደረባ፤ በድርጅቱ ገፅ ላይ፤ በዓለም ዙርያ በድረ-ገፆች ላይ

እንቅስቃሴ በማድረጋቸዉ እስር ላይ ያሉ አምደኞችን ይፋ የሚያደርግ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት በዚሁ ድረ-ገፅ ላይ፤ በዓለም ዙርያ በድረ-ገፅ እንቅስቃሴያቸዉ የታሰሩ የ 164 አምደኞች እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆኖ ይገኛል።
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት የቀድሞዉ ባልደረባ ኤድዋርድ ስኖዉደን፤ የአሜሪካን የስለላ ስራ ካጋለጠ በኃላ፤ የግለሰብ ምስጢር እንዳይፈትሹ እና እንዳይሰልሉ፤ የሚፈሩት በዓለማችን የሚገኙ አንባገንን መንግስት ብቻ እንዳልሆኑ ግልፅ ሆንዋል። ስኖዉድን ካጋለጠዉ የዩናይትድ ስቴትስን የስለላ ድርጅት ስራዎች መካከል፤ የስልክ ጥሪዎችን ማዳመጡን፤ የኤስ ኤም ኤስ መክቶችን፤ የኢሜል መልክቶችን እንዲሁም በድረ-ገፅ ላይ የሚገኝ የግለሰብ መረጃን እየፈለፈለ መሰለሉ ይገኝበታል።
የጓቲማላዋ « ዘ ቦብስ»ድርጅት ታዛቢ እና የግለሰብ የሃሳቦች ባለቤት ላይ ምሁር እና ጠበቃ ሪናታ አቪላ እንደሚሉት፤ የግለሰብን ሚስጢር በድረ-ገፆች ላይ እየተከታተሉ፤ ማህበረሰባችን በማዳከም ለድረ-ገፆች ያለንን እምነት የሚያጠፉትን የመንግስት ቅጥረኞች መታገልና ፍርድ ፊት ማቅረብ ይኖርብናል፤ ሲሉ ተናግረዋል።
« ዘ ቦብስ» የተሰኘዉ የዶቼ ቬለ የሽልማት ቡድን፤ ታዛቢ አርሽ አብዳፖር እንደገለጹት፤ በዩኤስ አሜሪካና ሌሎች ዲሞክራሲ ሰፈነባቸዉ በሚባሉ ሃገሮች፤ የሚገኙ ህዝቦች መንግስት ግለሰባዊ ሚስጥራችን ከሚሰልል ይጠብቀናል ብለዉ እምነታቸዉን ሲጥሉ፤ በኢራን የሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በበኩላቸዉ፤ በድረ-ገፆች ላይ የሚገኙ የግል ሚስጥራዊ መረጃቸዉ እንዳይሰለል የገዛ ጉልበታቸዉን ተጠቅመዉ ማስከበር እንዳለባቸዉ ተረድተዋል። እንደ አብዳፑር ፤ የአሜሪካኑ የስለላ ድርጅት የቀድሞ ባልደረባ ስኖዉደን አመኔታ መጣል ብቻ መሰረታዊ ነገር እንዳልሆነ አሳይቶናል። እናም እዚህ ላይ በኢንተርኔት አጠቃቀምና ፍተሻ ላይ አንድ በግልጽ የተቀመጠ የቁጥጥር አሰራር እና እምነት ምን ሊመስል ይችላል ስል እራሴን እጠይቃለሁ፤ ሲሉ አብዳፑር ያስረዳሉ።


በዚህም « ዘ ቦብስ» የሽልማት ቡድን ገምጋሚዎች ፤ በድረ ገፆች ላይ የአሰራር ህግ እስካልቀረበ እና እስከ ሌለ ድረስ የኢንተርኔት እና የኢንተርኔት አምደኞች እራሳቸዉን የሚያስጠብቁበት የራሳቸዉ ስልት መፈለግ ይኖርባቸዋል።
የሚታወቅ መረጃን ደግመዉ የሚያወጡ ሚዲያዎች፤ እዉነትን በግልፅ ይፋ የማያወጡ ከሆነ፤ አምደኞች ማንነታቸዉን ሳያሳዉቁ፤ ትክክለኛዉን ገልጾ በማዉጣት ምርመራን (ሳንሱርን) ሊታገሉ ይችላሉ።
« ዘ ቦብስ» የተሰኘዉ የዶቼ ቬለ የምርጥ ድረ-ገፅ ሽልማት መድረክ ፤ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በዓለም ዙርያ ባለዉ ድረ-ገፅ ትስስር መድረክ፤ ለሃሳብ ነጻነት በግምባር ቀደም ምሳሌነት የሚጠቀስን፤ የኢንተርኔት ፕሮጄ እና ተጠቃሽ የሚሆኑ ሃሳቦችን ማወዳደር ይጀምራል። ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረግ ዉድድር፤ በ14 የተለያዩ ቋንቋዎች ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ዉድድሩ አንድ ወር ይዘልቃል።
አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic