የማዳጋስካር የምርጫ ጉዞ | አፍሪቃ | DW | 24.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማዳጋስካር የምርጫ ጉዞ

በማዳጋስካር ከአራት ዓመት ተኩል በፊት መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ ደሴቲቱ እከፋ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። በሀገሪቱ ይካሄዳል የተባለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በተደጋጋሚ መተላለፉ የሚታወስ ነው።

ሁንና፣ እንዳዲስ የተዋቀረው የምርጫ ጉዳይ ተመልካች ፍርድ ቤት በተወዳዳሪነት ሊቀርቡ የነበሩ የሦስት አከራካሪ ዕጩዎችን ስም፣ እአአ ከ 2009 ዓም ወዲህ ሥልጣኑን የያዙት የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዚደንት አንድሬይ ራዦሊናን ስም ጭምር ፣ ከተወዳዳሪዎች ዝርዝር የሰረዘበት ድርጊት የሀገሪቱን ቀውስ በማብቃቱ ሂደት ላይ እንደ መጀመሪያ ርምጃ ተቆጥሮዋል። እና ይህ ሕዝቡን በርግጥ አዲሱን ፕሬዚደንቱን መምረጥ ያስችለው ይሆን? ሁሉ የሀገሪቱ ሕዝብ ግንይህ ይሆናል ብሎ አያምንም።
ከአንድሬይ ራዦሊና ሌላ በምርጫ እንዳይወዳደሩ የተከለከሉት የቀድሞው ፕሬዚደንት ማርክ ራቫሎማናና ባልተቤት ወይዘሮ ላሎ ራቫሎማናና እና ዲድየ ራትሲራካ ናቸው። ራዦሊና በ2009 ዓም ራቫሎማናናን ከሥልጣን እንዲለቁ ከገፋፉ እና እኒህም ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከሸሹ በኋላ የሽግግሩን መንግሥት በመምራት ላይ ይገኛሉ። ሀገሪቱም ከዚያን ጊዜ ጀምራ ከቀውስ የምትወጣበትን መላ በማፈላለግ ላይ መሆንዋን በአንታናናሪቮ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ባለሙያ መምህር ኤሪክ ራኮቶአሪሶ ቢገልጹም፣ ይኸው ጥረትዋ ሊሳካ እንዳልቻለ ይናገራሉ፣ ለዚህም ምክንያቱ ይላሉ፣


« የምርጫው ዕለት አንዴ የማዳጋስካር የሽግግር ጊዜ ፕሬዚደንት ራዦሊና እና በደጋፊዎቻቸው፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ራቫሎማናና ንቅናቄአቸው፣ ማለትም፣ ሁለቱ ዋነኞቹ ተዋናዮች በፖለቲካው ሂደት ላይ በደቀኑት ፖለቲካዊ እንቅፋት የተነሳ በተደጋጋሚ መተላለፉ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል። »
እአአ ለሀምሌ 24፣ 2013 ዓም ታቅዶ የነበረው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንዳይደረግ ያሰናከሉትም እነዚሁ ሁለት ግለሰቦች እንደነበሩ የሚታወስ ነው። እርግጥ ፣ ከብዙ ማመንታት በኋላ በምርጫው በዕጩነት ላለመቅረብ ተስማምተው ነበር፣ ይሁንና፣ ማርክ ራቫሎማናና ባልተቤታቸው ላሎ በዕጩነት እንዲቀርቡ ካደረጉ በኋላ ራዦሊናም ምንም እንኳን የዕጩዎች ምዝገባ ቢያልፍም ለምርጫው በተወዳዳሪነት ተመዝግበዋል። ላሎ ራቫሎማናናም ግን በዕጩነት ለመቅረብ የተጠየቀውን ቅድመ ግዴታ ሳያሟሉ ነው የቀሩት። ለፕሬዚደንታዊው መርጫ በዕጩነት መቅረብ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ከምርጫው ቀደም ብለው በሚገኙት ስድስት ወራት ውስጥ በማዳጋስካር የኖር መሆን አለበት፣ ላሎ ራቫሎማናና ግን ከባለቤታቸው ማርክ ጋ በበደቡብ አፍሪቃ ነበር ነዋሪነታቸው። ዕጩነታቸው የታገደባቸው ሦስተኛው ተወዳዳሪ ዲድየ ራትሲራካም እስከ ጥቂት ጊዜ በፊት ድረስ ፈረንሣይ ሀገር ነበር በስደት የኖሩት።
ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ፣ በተለይም፣ የደቡባዊ አፍሪቃ መንግሥታት የልማት ትብብር ድርጅት፣ በምሕፃሩ ሳዴክ፣ ራዦሊና፣ ላሎም ሆኑ ራትሲራካ በዕጩነት የሚሳተፉበትን ምርጫ እንደማይቀበሉ እና እንደማይደግፉ በተደጋጋሚ ነበር ያስታወቁት። በሳዴክና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ነበር አዲሱ የምርጫ ጉዳይ ተመልካች ፍርድ ቤት ሦስቱን ዕጩነት የሻረው። ይህ ውሳኔው ከብዙ ጊዜ ወዲህ

Former Madagascar head of state Albert Zafy (L) speaks during the opening ceremony on November 3, 2009 of a meeting with leaders of Madagascar's four main political groupings kicking off a fresh round of internationally-sponsored talks aimed at finding a way out of the Indian Ocean island's months-old crisis. Andry Rajoelina, a 35-year-old former disc jockey, toppled Madagascan President Marc Ravalomanana with the army's backing on March 17 but has since failed to win the recognition of the international community. The coup came as a result of months of sometimes violent demonstrations which left the island in diplomatic and institutional limbo, with parallel adminstrations claiming legitimacy. AFP PHOTO/Gregoire POURTIER (Photo credit should read GREGOIRE POURTIER/AFP/Getty Images)

የማዳጋስካር የቀድሞ ፕሬዚዳንት አልበርት ዛፊ

የተስተጓጎለው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚደረግበትን መንገድ እንደሚያመቻች ብዙዎች ተስፋ ቢያደርጉም፣ የፖለቲካ ተንታኙ ቱአቪና ራላሙቡማሀ አብዝተው ይጠራጠሩታል።
« ብዙ ጊዜ ነበር ምርጫው ይደረጋል ብለን ማዳጋስካር ውስጥ ብሩሑን ተስፋ አሳድረን የነበረው። እአአ ከሀምሌ 24 በፊት ምርጫው በርግጥ ይደረጋል ? አይደረግም? ብለን ጠይቀን ነበር። አሁንም የምርጫው ዕለት ሲቆረጥ ይህንኑ ጥያቄ እንደገና መጠየቃችን የማይቀር ነው። »
የማዳጋስካር የምርጫ ኮሚሽን ኃላፊ ወይዘሮ ቤአትሪስ አታላ ሀገሪቱን ከምትገኝበት ቀውስ ለማላቀቅ መፍትሔው ምርጫ መሆኑን ያምናሉ።
« ማዳጋስካርን ማዳን ከተፈለገ ጥሩ ምርጫ ማዘጋጀት ነው፣ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ተዓማኒ እና ግልጽ ምርጫ ማዘጋጀት ብቻ ነው ። »
ኮሚሽናቸው የመራጮችን እና የተመራጮችን ስም ዝርዝር በማዘጋጀት ላይ ሲሆን፣ ዝርዝሩ የዓለም አቀፉን ማህበረ ሰብ ይሁንታ ካገኘ ምርጫውን ከመካሄድ የሚያከላክለው ጉዳይ እንደሌለ ቤአትሪስ አታላ ገልጸዋል። እንዳአታላ ግምት፣ ምርጫው የፊታችን ጥቅምት ሊደረግ ይችል ይሆናል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን አንዳንድ ለምሳሌ ከምርጫ የታገዱት ዕጩዎች ደጋፊዎች ሌላ ተተኪ ዕጩ ይሰይማሉ? በተቀናቃኞቹ ወገኖች መካከልስ ግጭት ይፈጠር ይሆን? ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይኖርባቸዋል። ይህም የሚያሳየው የማዳጋስካር የምርጫ ጉዞ ገና አለማብቃቱን ነው።

ፍሬዴሪከ ሙለር/አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን

Audios and videos on the topic