የማሊ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዕጩዎች | አፍሪቃ | DW | 29.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ዕጩዎች

በማሊ ሐምሌ 21፣ 2005 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተካሂዶዋል። በማሊው ምርጫ በዕጩነት የቀረቡት ዋነኞቹ ተወዳዳሪዎች እነማን ናቸው?

ውዝግብ ባዳቀቃት ምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ማሊ ውስጥ ሕዝቡ ትናንት ሐምሌ 21፣ 2005 ዓ ም አዲስ ፕሬዚደንት ለመምረጥ ወደየምርጫ ጣቢያዎቹ ወጥቶዋል። ይሁንና፣ ብዙዎቹ የማሊ ዜጎች ምርጫው እንዲህ በጥድፊያ እንዲካሄድ መወሰኑን ትክክለኛ ሆኖ አላገኙትም። ምክንያቱም የፀጥታው ሁኔታ አሁንም ባልተረጋጋው በሰሜናዊ ማሊ የመራጩን ደህንነት ማረጋገጥ መቻሉ አሁንም አስተማማኝ አይደለም። ይኸው አካባቢ ካለፈው ዓመት ወዲህ በመጀመሪያ የአዛዋድ ነፃ አውጪ ንቅናቄ በሚባለው ኤምኤን ኤልኤ በኋላም በተለያዬ እሥላማዊ ቡድኖች ተይዞ ነበር የቆየው። ይህ ሁኔታ ከሞላ ጎደል ሊያበቃ የቻለው ጥር 2005 ዓም የፈረንሣይ ጦር ጣልቃ በገባበት እና ብዙውን አካባቢ ካስለቀቀ በኋላ ቢሆንም፣ አሁንም ያካባቢው ፀጥታ ስጋት ይታይበታል። የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚሁ ምርጫ በተወዳዳሪነት ለመቅረብ ማመልከቻ ካስገቡት መካከል የ 28 ዕጩዎች ጥያቄ ተቀብሎዋል።


ለምርጫው ከሚወዳደሩት 28 ዕጩዎች መካከል ብዙዎቹ የቀድሞ ፖለቲከኞች መሆናቸው ታውቋል። ከጥቂት ቀናት በፊት ባበቃው የምርጫ ዘመቻ ወቅት አንዱ ዕጩ የሆኑት የ61 ዓመቱ ሞዲቦ ሲዲቤ ደጋፊዎችን ናቸዉ። ሲዲቤ እ ጎ አ በ 1990 ዓም የህገሪቱ ፕሬዚደንት የነበሩት የአልፋ ኡማር ኮናሬ፣ በኋላም መጋቢት 2012 ዓም ከሥልጣን የተወገዱት የቀድሞው ፕሬዚደንት ቱማኒ ቱሬ የቅርብ ነበሩ። ከሳቸው ሌላ ኢብራሂም ቡባካር እና ሱማይላ ሲሴ በምርጫው ደህና ዕድል እንዳላቸው ይገመታል። እነሱ እና ሌሎች ብዙዎቹ ዕጩዎች ለማሊ የፖለቲካ መድረክ አዲሶች አይደሉም። ይላሉ በመዲናይቱ ባማኮ የሚገኙት የጀርመናውያኑ የፍሪድሪኽ ኤበርት ተቋም ኃላፊ አኔተ ሎማን።
« ትክክል ነው፣ ቀደም ሲል የተጠቀሱት ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሙሉ የቀድሞ መንግሥታት ፖለቲካዊ ተቋሞች ተወካዮች፣ ጠቅላይ ሚንስትር ወይም ፕሬዚደንት ሆነው ያገለገሉ ነበሩ። ለአዲስ የፖለቲካ ሥርዓት የቆሙ አዳዲስ ፖለቲከኞች አይደሉም። ሲታሰብ ግን እንዲህ ባጭር ጊዜ ውስጥ በሀገሪቱ የፖለቲካው መድረክ የሚንቀሳቀሱትን በጠቅላላ መቀየር ይቻላል ተብሎ በፍፁም የማይጠበቅ ነው። »
እንደሚታወቀው እጎ አ መጋቢት 22፣ 2012 ዓም በ,,ሀገሪቱ መፈንቅለ መንግሥት በመካሄዱ ምክንያት ነበር ምርጫው ያስፈለገው፣ ያኔ በሻለቃ አማዱ ሳኖጎ የተመሩ ወታደሮች 10 ዓመታት የሀገሪቱን ፕሬዚደንትነት ሥልጣን ይዘው የቆዩትን አማዱ ቱማኒ ቱሬን ከሥልጣን አነሱ።

ይህ ከሆነ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግፊት በማሊ የሽግግር መንግሥት ተቋቋመ። ግን የሽግግሩ መንግሥስት መጀመሪያ ላይ ደካማ ስለነበረ መፈንቅለ መንግሥቱን በተከተሉት ወራት የሀገሪቱን ኤኮኖሚያዊ ሁኔታ ማስተካከልም ሆነ ፖለቲካዊ መረጋጋት ማስገኘት ሳይሳካላለት ነበር የቀረው። በዚህ ሁኔታ ቅር የተሰኙት የማሊ ዜጎች በነገው ዕለት አዲስ ፕሬዚደንት መመረጥ በመቻላቸው ደስተኞች ናቸው። በዚህም የተነሳ ዕጩዎቹ የቀድሞ ፖለቲከኞች መሆናቸው በባማኮ እንደምተኖረው ቢንቱ ኩሊባሊ ብዙዎቹን የማሊ ዜጎች አላስጨነቀም።
« ምርጫው ለኔ በጣም ወሳኝ ነው። እዚህ ያለነው ላችንም የሽግግሩ መንግሥት እንዲያበቃ ነው የምንፈልገው። ሙሉ ሥልጣን ያለው እና ማሊን ከምትገኝበት ቀውስ የሚያላቀቅ ፕሬዚደንት እንፈልጋለን። »
ብትልም፣ ድምፅዋን ለለየትኛው ዕጩ እንደምትሰጥ ለመጠቆም አልፈለገችም። በቢንቱ አንፃር የሬፓብሊኳና የዴሞክራሲ ህብረት የሚባለው የሱሜይላ ሲሴ ፓርቲ የክብር ፕሬዚደንት ማሊክ ቱሬ የ 64 ዓመቱ ሲሴ ድል እንደሚቀዳጁ በርግጠኝነት በመግለጽ ዕጩዋቸው እንዲያሸንፉ ለመርዳት ጠንካራ ዘመቻ እንዳካሄዱ ነበር ያስታወቁት።

Titel: DW_Mali-Wahlkampf7: Werbung für Präsidentschaftskandidat Ibrahim Boubacar Keïta Schlagworte: Mali, Wahlen, Wahlwerbung, Ibrahim Boubacar Keïta Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Katrin Gänsler Wann wurde das Bild gemacht?: 20. Juli 2013 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Gao, Mali Rechteeinräumung: Hiermit räume ich der Deutschen Welle das Recht ein, das/die von mir bereitgestellte/n Bild/er zeitlich, räumlich und inhaltlich unbeschränkt zu nutzen. Ich versichere, dass ich das/die Bild/er selbst gemacht habe und dass ich die hier übertragenen Rechte nicht bereits einem Dritten zur exklusiven Nutzung eingeräumt habe. Katrin Gänsler/katrin.gaensler@gmail.com

የቡባካር ኬታ የምርጫ ማስታወቂያ


« ሲሴ ለብዙ ጊዜ የገንዘብ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። በሥልጣን በቆዩባቸው ስድስት ዓመታትም ውስጥ ጥሩ የበጀቱን ሚዛን ጠብቀው የቆዩ ብቸኛው ሚንስትር ነበሩ። እሳቸውን ከተኩት መካከል አንዳቸውም የሳቸውን ዓይነት ውጤት ያስመዘገበ የለም። »

ከሲሴ ይበልጥ በምርጫው ዘመቻ ወቅት ይበልጥ ጎልተው የታዩት ዕጩ ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር እና የምክር ቤት ፕሬዚደንት የነበሩት የ68 ዓመቱ ኬታ ጠንካራ ከሚባሉት ዕጩዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ። ኬታ በምርጫው ዘመቻ ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር በተደጋጋሚ ያነሱት ሀሳብ ማሊ የማትከፋፈል ሀገር መሆንዋን እና የሀገሪቱን አንድነት ጠብቆ ማቆየት የተሰኘውን ነው። ይህ ብዙ መራጮችን ድምፃ ሊያስገኝላቸው ይችላል ተብሎ ይገመታል። ሐምሌ 21፣ 2005ዓ ም በሚደረገው የመጀመሪያው ዙር ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ግን ኬታም ሆኑ ሲሴ ወይም ሲዲቢ እና ሌሎቹ አብላጫውን ድምፅ አግኝቶ ያሸንፋል ተብሎ አይጠበቅም። አንዱም ካላሸነፈ ሁለተኛ ዙር ምርጫ የፊታችን ነሐሴ 5፣ 2005 እንዲደረግ ዕቅድ ተይዞዋል።

ማርቲን ጌንስለር/አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic