የሙዚቃ ሊቁ ቤትሆፈን እና ቦን ከተማ | ባህል | DW | 13.09.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሙዚቃ ሊቁ ቤትሆፈን እና ቦን ከተማ

የራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በቦን ከተማ ባለፈዉ እሁድ ከቀትር ጀምሮ ለአንድ ወር የሚዘልቅ ታላቅ የክላሲክ ሙዚቃ በአል በመደረግ ላይ ነዉ። የራይንን ወንዝ ተንተርሳ ያለችዉ ቦን ከተማ የራድዮ ጣብያችን፣ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ቅርንጫፍ ቢሮ

default

ሉድቪግ ቤትሆፈን

የጀርመኑ ፖስታ ቤት ዋና ጽ/ቤት፣ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ዋና መቀመጫ ብቻ ሳትሆን በአለማችን በክላሲክ ሙዚቃ ታላቅ ሊቅ የሆነዉ ጀርመናዊዉ የቤት ሆፈንም የትዉልድ ቦታ ናት። ታድያ ቦን ለዚሁ የሙዚቃ ሊቅ ማስታወሻ በያመቱ የሙዚቃ ድግስዋን በማድረግ ቤትሆፈንን ታስባለች።
በ1770 እስከ 1827 ድንቅ የሙዚቃ ስራዉን በተለይ የክላሲክ ሙዚቃ በመጻፉ አሁን ድረስ በተለይ በአዉሮጻዉያኑ ዘንድ ተደናቂነትን ያተረፈዉ ጀርመናዊዉ ሉድቪግ ቤትሆፈን ትዉልዱ እዚህ በቦን ከተማ ነዉ። በርካታ የክላሲክ ሙዚቃ አፍቃሪዎች ከተለያዩ የአለም አገራት በመምጣት የቤትሆፈንን የትዉልድ ቦታ የተማረበትን ትምህርት ቤት እና ዩንቨርስቲ እንዲሁም የኖረበትን ቤት ይጎበኛሉ። የቤትሆፈን ቤት «ቤቶፈን ሃዉስ» በማለት የሚጠሩት ሙዝየም እዚህ በቦን ከተማ የቤትሆፍን ስራዎች እና ቁሳቁሶች የሚታዩበት በአለም ታዋቂ የሆነ እግዚቢሽንም ነዉ።
ባለፉት በተደረጉት የአለም ጦርነነቶች ሳፍረስ ጥንታዊ ታርኩን ይዞ የተቀመጠ ጥንታዊ ከሚባሉት ቤቶች ዉስጥ በቦን የሚገኘዉ የቤት ሆፈን ቤት አንዱ ነዉ። በ18ኛ ምዕተ አመት መጀመርያ ላይ ነዉ የተገነባ ቢሆንም የቤቱ መጀመርያ መሰረት የተጣለዉ እና ቤቱ የመጀመርያ ምሶሶ የተጣለዉ በ 12 እና 13 ምዕተ አመት እንደሆነ ይነገራል። ይህ ጥንታዊ የቤትሆፈን መኖርያ ቤት ዛሪ ከአለም አገራት የሚመጡ ቱሪቶች ቦን ከተማን ረግጠዉ የሙዚቃ ሊቁን ቤት ሳይረግጡ አይመለሱም።

Geburtshaus von Ludwig van Beethoven in Bonn

ቤትሆፈን የተወለደበት ቤት በቦን ከተማ


የቤትሆፈን አባት ምንም እንኳ የአልኮል መጠጥ ሱሰኛ እንደነበሩ ቢነገርም የሞዛርትን ሙዚቃ እጅግ በማድነቃቸዉ ምክንያት ልጃቸዉ ቤትሆፈን በሙዚቃ ትምህርቱ እንዲቀጥል ከህጻንነቱ ጀምሮ ከፍተኛ ግፊት ያደርጉበት እደነበር ይነገራል። ቤትሆፈን ባለበት ከባድ ግፊት ለአባቱ ፍቅር ባይኖረዉም እናቱን እጅግ ይወድ እንደነበረም ተገልጾል። ቤትሆፈን በባቱ አስተማሪነት ከትምህርት ቤት ቀርቶ የሙዚቃ ትምህርቱን ማለት የፒያኖ ጨዋታ ትምህርቱን እቤት ዉስት ቀጠለ።
የቤትሆፈን አባት ልጃቸዉ ቤትሆፈን ሙዚቂ ሲያስተምሩ ቆይተዉ እጅግ መሻሻሉን ቢያዩ በቂ የሙዚቃ እዉቀት ያለዉ አስተማሪ በመቀጠል እንዲያስተምረዉ ፈለጉ። ቤትሆፈን በድሜዉ በጣም ጥሩ የፕያኖ ተጫዋች ቢሆንም ሌላ የሙዚቃ አስተማሪ ተፈልጎለት ትምህርቱን መከታተል ቀጠለ። ቤትሆፈን አስራ አራት አመት ሲሞላዉ እጅግ ጥሩ ፕያኖ በመጫወቱ ስራ አግኝቶ ደምወዝተኛ ሆነ። ቤትሆፈን ትምህርቱንም ስራዉንም በጥሩ በመከታተል በመቀጠል በጀርመን በዝያን ወቅት ታዋቂ የሆነዉ ሞዛርት ጋር ወደ አዉስትርያ ቪየና ሄዶ የሙዚቃ ትምህርቱን መከታተልን ፈለገ። ወድያዉም ትህርቱን አዉስትራያ ለማድረግ ወስኖ ወደ ቪየና ሄደ።
ቤትሆፈን የሙዚቃ እዉቀቱን ለማጠናከር ወደ ሞዛርት ጋር ወደ አዉስትርያ ቢየና ቢሄድም እንዳሰበዉ ትምህርቱን እንደፈለገዉ መማር አልቻለም። እናቱ በጠና በመታመማቸዉም ወደ ቦን ከተማ ተመለሰ። ቤትሆፈን በእናቱ ሞቱ እጅግ እንዳዘነ ይነገራል ። ቤትሆፈን የሙዚቃ ትምህርቱን በቦን ዩንቨርስቲ ቀጥሎ በትምህርት ላይ ሳለ ፍሪንች ሪቮሉሽን የፈረንሳይ አብዮት ንቅናቂ በሚል አንድ የሙዚቃ ሲንፎኒ ጻፈ። ይህ የሙዚቃ ስንፎኒ እስካሁን ድረስ እጅግ ተደናቂ እንደሆነ ነዉ።
የሙዚቃ ሊቁ ጀርመናዊዉ ሉድቢግ ቤትሆፈን በአምስት አመቱ የጀመረዉን የጆሮ ህመም በሽታዉን በደንብ ባለማስታመሙ እና ባለመከታተሉ ብቻ በጎልማሳ ዘመኑ ፍጹም መስማት ተሳነዉ። ይህን የሙዚቃ ሊቅ ድንቅ የሚያደርገዉ እና ከሊሎች የሙዚቃ ሊቆች ለየት የሚያደርገዉ የሚጽፋቸዉ የሙዚቃ ኖታዎች እንዲሁም የሚደርሳቸዉ ሙዚቃዎች በስሜት እንጂ አድምጦት ባለሞኑ ነበር። የቤትሆፈን ስራዎች የቤትሆፈን ፎቶ የቤትሆፈን በምስል ተቀርጾ እዚህ ቦን በሚገኘዉ በቤትሆፈን ሙዝየም ይሸጣል። የቦን ነዋሪዎችም ቤትሆፈን የነበረበት ከተማ በመኖራቸዉ ወይም በመወለዳቸዉ ሲኮሩ ይታያል።
ቤትሆፈን በመጨረሻ የህይወቱ ዘመንም በተለያዩ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች በዮንቨርስቲ የሙዚቃ አስተማሪም ነበር። ቤትሆፈን ትዳር ሳይዝ ልጅ ሳይተካ ነዉ ይህችን አለም ያለፈዉ ምንም እንኳ በኖረበት ዘመን ሴቶችን አፍቅሮ ትዳር ሳይሳካለት እንደቀረ የሚገልጹ ጽሁፎች ቢኖሩም። ቤትሆፈን በሃምሳ ሰባት አመቱ በደረሰበት የጉበት በሽታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። በጥንት ዘመን ኦስትርያ እና ጀርመንም አንድ ስለነበሩ በተለይ ቤትሆፈን በሞዛርት ስራ በመደነቅ የሞዛርትን ስራ ለማየት ወደ ኦስትርያ ይሄድ እንደነበረ ዘገባዎች ያሳያሉ። ቤትሆፈን ከሞዛርት ትንሽ ለየት ያደርገዉ መስማት ተስኖት ድንቅ የሙዚቃ ኖታ በመጻፉ ቶሎ አድናቂዎችን ሲያገኝና ሲጠቀም ሞዛርት ግን ስራዎቹ በነበረበት ዘመናት ይህን ያህል ተደናቂነትን ሳያገኙ ቆይተዋል።

Beethoven Bonn

በሙንስተር አደባባይ ላይ ያለዉ የቤትሆፈን ሃዉልት

ሞዛርት ስራዎቹን ለትዉልድ አስተላልፎ በሞዛርት ሙዚቃ አሁን በርካታ የሙዚቃ ቀማሪዎች እና የፒያኖ ተጫዋቾች ቢከብሩበትም ሞዛርት በህይወት ዘመኑ ደህይቶ ገንዘብ አጥቶ በሞተም ግዜ የሚቀብረዉ አጥቶ የአገሩ መዘጋጃ ቤት እደቀበረዉ ባለፈዉ ሁለት አመት፣ በቪየና የሞዛርት ሁለት መቶ ሃምሳኛ አመት ሲከበር ተገልጾአል። ሞዛርት ይህን አለም አልፎ ከሁለት መቶ ሃምሳ አመታት በኻላ ሙዚቃዎቹ ድንቅ ተብለዉ ህያዉ ሆነዉ ህዝቡ በኩራት በያመቱ የትዉልድ ቀኑን በማሰብ ስራዉን ለታዳጊዉ ሙዚቃ አፍቃሪ መማሪያ ሆኖ ይጠቀምበታል። የቦን ከተማችንም በያመቱ የቤትሆፍን ድግስ በተሰኘ ለአንድ ወር የሚዘልቅ ሲንፎኒ ለሙዚቃ አፍቃሪዎቹ ያቀርባል። በዚህ መረሃግብር ላይ የተለያዩ የአዉሮፓ አገሮች የቤትሆፈን ሙዚቃን በመስራት ዝግጅታቸዉን ያቀርባሉ። በቦን ከተማ እንብርት ላይ በሚገኘዉ በሙንስተር አደባባይ ላይ የቆመዉ የቤትሆፈን ሃዉልት አጠገብ የፒያኖ ተጫዋቾች ሰሞኑን የቤትሆፈንን የድግስ ወር በማስመልከት ዳሳቸዉን ዘርግተዉ ፒያኖ ይጫወታሉ። በዚህ በራድዮ ጣብያችን ህንጻ ዉስጥም በመግቢያዉ አካባቢ በዚሁ የቤትሆፈን ማስታወሻወር በቀን ቢያንስ አንዱ ሁለቴ የቤትሆፈንን የሙዚቃ ስራ በፒያኖ የሚጫወት ሙዚቀኛ ይታያል።