የመካሕ አደጋና ሐጂ | ዓለም | DW | 17.09.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የመካሕ አደጋና ሐጂ

የሞቱት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ-ስምንት ደርሷል።በመቶ የሚቆጠሩ ቆስለዋል።ለሐጂ የሚደረገዉ ጉዞና ፀሎት ግን አልታጎለም።በየዓመቱ እንደሚሆነዉ ሁሉ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ ሐገራት ሙስሊሞች ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:52
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:52 ደቂቃ

የመካሕ አደጋና ሐጂ

ባለፈዉ ሳምንት በመካዉ አል-ሐራም መስጊድ ላይ ግዙፍ ክሬን በመዉደቁ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸዉና መቁሰላቸዉ በዘንድሮዉ የሐጂ ጉዞ ላይ ያሳረፈዉ ተፅዕኖ ብዙም ያለ አይመስልም።ባለፈዉ ሳምንት በደረሰዉ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አስራ-ስምንት ደርሷል።በመቶ የሚቆጠሩ ቆስለዋል።ለሐጂ የሚደረገዉ ጉዞና ፀሎት ግን አልታጎለም።በየዓመቱ እንደሚሆነዉ ሁሉ ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተለያዩ ሐገራት ሙስሊሞች ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል።ጉዞዉን የታዘበዉ ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic