የመሬት መቀራመት እና መከላከያ መመሪያው | ABOUT DW | DW | 14.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ABOUT DW

የመሬት መቀራመት እና መከላከያ መመሪያው

128 የአገር መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች የመሬት መቀራመት ከሚያስከትለው ችግር ለመከላከልና የምግብ ዋስትናቸውንም ለማረጋገጥ የተ መ የምግብ እና የዕርሻ ድርጅት (FAO) ባለፈው አርብ በሮም ከተማ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ በአንድ ድምፅ መመሪያውን አፅድቀዋል።

Skeptisch betrachtet ein äthiopischer Anwohner das schwere Gerät, das die Inder zum Roden der Anbauflächen für Weizen,Baumwolle und Zuckerrohr

የመሬት መቀራመት በኢትዮጵያ

መመሪያው ስለ መሬትና ስለ አሣ ይዞታ አጠቃቀም ፣እንዲሁም፣ ስለ ደኖች አያያዝ በዝርዝር አብራርቶዋል። መሬት ለባለሀብቶች የሚሰጥበት አሰራር ግልፅ መሆን ፣ የሕዝቡ አብሮ የመወሰን መብት መከበር፣ በተለይ ግን የአነስተኞቹን ገበሬዎች አቋም እንዲጠናከር ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን መመሪያው አሳስቦዋለ። ባቤቴ ቬርማን ከተ መ የምግብ እና ዕርሻ ድርጅት (FAO)የአየር ንብረት፣ የኃይል እና የአጠቃቀም መብት ጉዳይ ተጥሪ እንደሚሉት፣ እነዚህ ገበሬዎች ይፋ ያልሆነ የመሬት ተጠቃሚነት መብት እንጂ ሕጋዊ የባለቤትነት ሰነድ የላቸውም።

« ዋናው ነገር መሬቱን የመጠቀም መብት እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች በሰዎች ዘንድ እውቅና ማግኘት ይኖርባቸዋል፤ እነዚህም ሰዎች የሀብት ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሊኖራቸው ይገባል። አንድ ሰው ምናልባት ጠቀም ያለ ገንዘብ ስላለው ወይንም ተፅዕኖ ማሳረፍ ስለቻለ ብቻ፤ የባለቤትነት መብታቸውን በአንድ ጊዜ ሊነጠቁ አይገባም።»

aruturis PR-Mann Birinder Singh: Win-Win für Äthiopiens Farmer und Karuturi Copyright. Schadomsky/DW

የህብድ ባለሀብቶች

በምህፃሩ ILC የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ያወጣው መዘረዝር እንደሚያሳየው፣ እኢአ ከ2000 ዓም ጀምሮ 83 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ለባለ ሀብቶች ተሸጠዋል ወይም በኪራይ ተይዞዋል። ከዚህም መካከል ብዙው መሬት የሚገኘው በአፍሪቃ ነው ሲሆን፣ ሱዳን ፣ኢትዮጵያ፣ ሞዛምቢክ፣ ታንዛኒያ እና ዛምቢያ በምሳሌነት ተጠቅሰዋል። በአፍሪቃ መሬት በኪራይ ወይም በግዢ ከያዙት ባለሀብቶች መካከል ህንድ ፣ ቻይና እና ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ሲሆን ፣ የILC ተጠሪማይክል ቴይለር እንደገለጹት እነዚህ ሀገሮች ሳይቀሩ በአዲሱ መመሪያ ላይ ተስማምተዋል። በአሁኑ ሰዓት መንግስታት በባለሀብቶች አኳያ የሚከተሉት የመሬት ፖሊሲ ላካባቢው ሕዝቦች ከሚያስገኘው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ነው ILC የገለጸው። ባለሀብቶች ከአገሪቱ ትናንሽ ገበሬዎች ጋ ተባብረው ቢሰሩ ማህበረሰቡ ይበልጥ ተጠቃሚ ሊሆን ይችል ነበር ። ይሁንና፣ አሁን በርካታ አገሮች በአዲሱ መመሪያ አማካኝነት የገበሬዎችን መብት ለማስከበር እየሰሩ መሆኑን ቴይለር ገለጸዋል።

« እንደ ማዳጋስካር እና ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት መስጠት ጀምረዋል። ምንም እንኳን የሕጋዊ ሰነድን ያህል ክብደት ባይኖረውም። ማደጋስካር ውስጥ አንድ ገበሬ ለመሬቱ የምስክር ወረቀት ለማውጣት ይከፍለው የነበረው 600 ዶላር አሁን ወደ 15 ዶላር ቀንሶለታል።»

ይህ የምስክር ወረቀት ትናንሽ ገበሬዎች ወደፊት መሬታቸውን ይዘው እንዲቆዩ ይረዳል። ምክንያቱም ትላልቅ ባለሀብቶች ያካባቢውን ሕዝብ ከተጋፉ፤ የገበሬዎች ክስረት እጥፉን ነው የሚሆነው። በአንድ በኩል እራሳቸው ማምረት አይችሉም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙው ምርት ለውጭ ገበያ ይላካል። እና የጀርመናውያኑ አለም አቀፍ እና ያካባቢ ጥናት ተቋም ተንታኝ ኬርስቲን ኖልተ እንደገለጹት፣ ባለሀብቶች ያልታረሰ መሬት ነው የሚፈልጉት የሚለው አነጋገር ግራ የሚያጋባ ነው።

Noch stehen die lokalen Bauern dem indischen Groß-Investment, exemplifiziert durch die schweren Rodungsmaschinen, etwas skeptisch gegenüber Copyright liegt bei Ludger Schadomsky/DW Aufnahmedatum für alle Fotos: 13.8.2011 DW/Schadomsky

ገበሬዎች ከትላልቅ ባለሀብቶች ጎን ቆመው የሚሰሩትን ይመለከታሉ

« ባለሀብቶች የሚመርጡት መሬት ለም እና የተሟላ መሰረተ ልማት ያለውን ነው። ይህ ዓይነቱ መሬት ደግሞ ለወትሮው ብዙ ሕዝብ የሰፈረበት ነው። ያ ደግሞ የሕዝብ መፈናቀልን ያስከትላል ማለት ነው።»

የተ መ አገሮች አሁን በፈቃደኝነት የተስማሙበት መመሪያ የአካባቢውን ሕዝቦች ሁኔታ የሚያጠናክር እና በመሬት ፖሊሲ ላይ ግልጽነትን የሚያስገኝ የመጀመሪያ ርምጃ መሆኑን ጠበብት ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ መመሪያው የአነስተኞቹን ገበሬዎች የኑሮ ሁኔታ በተወሰነ ደረጃ እንዲሻሻል ድርሻ ሊያበረክት ይችላል ብለው ይገምታሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic