የመማሪያ መጽሃፍት ችግር በኢትዮዽያ | ኢትዮጵያ | DW | 04.01.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመማሪያ መጽሃፍት ችግር በኢትዮዽያ

በኢትዮዽያ የትምህርት ጥራት መውረድ መነጋገሪያ ከሆነ ሰንብቷል። ለዚህ ሀገራዊ የትምህርት ጥራት መውረድ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች የመማሪያ መጽሃፍት አለመኖር ወይም እጥረት አንዱ ነው።

default

ዘንድሮ ተማሪዎችን የገጠማቸው ችግር ደግሞ በአይነቱ የተለየ ሆኗል። የ11ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እስከአሁን የሚማሩባቸው መጽሃፍት የሉም። የመልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ያለመጽሃፍት አራት ወራት መቆያታቸው ሳይሆን ለፈተና ሊቀመጡ አራት ወራት መቅረቱ ነው -አሁን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳሰባቸው ያለው። መንግስት መጽሃፍቱን ሊያትሙ ጨረታውን ካሸነፉ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በተፈጠረ ችግር የተነሳ እንደሆነና አሁን ግን ችግሩ ተቀርፎ የታተሙት መጽሃፍት ጅቡቲ እንደደረሱ ይገልጻል።

ታደሰ እንግዳው

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ