የመመረቂያ ፁሁፍ እና የሰውን ሀሳብ መስረቅ | ባህል | DW | 15.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የመመረቂያ ፁሁፍ እና የሰውን ሀሳብ መስረቅ

ሰሞኑን ጀርመኒያውያንን እያነጋገረ ካለ ጉዳይ አንዱ የጀርመን የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት የአኔተ ሻቫን ጉዳይ ነው።

Nordrhein-Westfalen/ ARCHIV: Ein gedrucktes Exemplar der Dissertation der heutigen Wissenschaftsministerin Annette Schavan (CDU) mit dem Titel Person und Gewissen steht in Duesseldorf an der Heinrich-Heine-Universitaet fuer eine Illustration in einer Bibliothek (Foto vom 15.10.12). Der Fakultaetsrat der Philosophischen Fakultaet der Heinrich-Heine-Universitaet beschaeftigt sich am Dienstag (22.01.13) in Duesseldorf in einer Sitzung mit der Frage, ob ein Verfahren zur Entziehung des Doktorgrades von Bundesbildungsministerin Schavan eroeffnet wird. (zu dapd-Text) Foto: Sascha Schuermann/dapd

Universität Düsseldorf eröffnet Plagiatsverfahren gegen Annette Schavan

ሻቫን ከ 30 አመት በፊት በፃፉት የዶክትሬት የመመረቂያ ፁሁፍ ላይ የሰውን ሀሳብ የራሳቸው አስመስለው በፁሁፋቸው አስፍረዋል በሚል ክስ፤ የዶክትሬት ማዕረጋቸውን ተገፈዋል። ይህም ከሚንስትርነት ስራቸውም ለመባረር ዳርጓቸዋል።

German Education Minister Annette Schavan makes a statement in Berlin February 9, 2013. Germany's education minister resigned on Saturday after being stripped of her doctorate over plagiarism charges, an embarrassment for her close confidante Chancellor Angela Merkel who is campaigning to win a third term in office this year. REUTERS/Tobias Schwarz (GERMANY - Tags: POLITICS)

አኔተ ሻቫን

እስካለፈው ሳምንት በጀርመን የትምህርት ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አኔተ ሻቫን፤ በተለይም ከትምህርት ጋ በተያያዘ መከሰሳቸው ይህም እስከ የዶክትሬት ማዕረግ መነጠቅና ከስራ መባረር መዳረጉ፤ ዮሀንስ ሀጎስ ለጉዳዩ የበለጠ ትኩረት ሰጥቼ እንድከታተለው አድርጎኛል ይላል። ወጣቱ በጀርመን ድሬስድን ዩንቨርስቲ በአሁኑ ሰዓት በውሃ ምንድስና ላይ ለ3ኛ ዲግሪው ( PHD) የመመረቂያ ጥናት እየፃፈ ይገኛል። ተሞክሮውን አካፍሎናል።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Hauptcampus der Universität Addis Abeba (AAU) Thema: Die Universität Addis Abeba (AAU) ist traditionell ein Hort der politischen Opposition. Die Proteste gegen die Wahlfälschungen 2005 wurden nicht zuletzt von Studenten auf die Straße getragen. Sicherheitskräfte patroullieren derzeit verstärkt auf dem Campus Schlagwörter: Universität Addis Abeba, University of Addis Ababa (AAU), Proteste 2005, Wahl Äthiopien 2010, Ethiopia 2010

የመጀመሪያው የኢትዮጲያ ዩንቨርሲቲ

ባለማወቅ፣ በቸልተኝነት ወይንም ይህ አጠቃላይ እውቀት ነው በማለት አንድን ሀሳብ ከሌላ ቦታ የመነጨ መሆኑን ያለመጥቀስ ሁኔታ ይታያል። ለመሆኑ መቼ ነው አንድ ሰው የራሱን ያልሆነን ጥናት ወይንም ሀሳብ ምንጭ ሳይጠቅስ አቀረበ የምንለው? በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሶይሲዮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት - ዶክተር የራስ ወርቅ አድማሴ በዚህ ላይ መልስ ሰጥተውናል።

ዶክተር የራስ ወርቅ በየጊዜው የተለያዩ የመመረቂያ ፁሁፎችን ማንበብ ግድ ይላቸዋል። አልፎ አልፎም «ይህን አረፍተ ነገር የት ነበር ያነበብኩት» የሚለው ጥርጣሬ ያድርባቸዋል።

የራስ ያልሆነን ጥናት እንደ ራስ አድርጎ ማቅረብ ፤ ማዕረግን እስከመነጠቅ እንደሚያደርስ በቅርብ ጊዜ እዚህ ጀርመን ውስጥ ብቻ በሁለት ፖለቲከኞች ላይ ታይቷል። የጀርመኗ ሚኒስትር የመመረቂያ ፁሁፍ ተመሳክሮ ስህተቱ የተገኘው ለ ሶስት አስርተ ዓመታት በመቀመጡ ነው። ይህም በኢትዮጵያ ይደረጋል። ግን ዶክተር የራስ ወርቅ እንደገለፁልን፤ ለሁሉም ፁሁፎች አይደለም።

የአንድን እጬ ተመራቂ ፁሁፍ ለማመሳከር ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ከባድ ያደርገዋል? ለዚህ እና ለሌሎች ጥያቄዎች ዶክተር የራስ ወርቅ ጠቃሚ ሀሳቦች አካፍለውናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች