የሕንድና የአፍሪቃ ጉባኤ | ኢትዮጵያ | DW | 20.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሕንድና የአፍሪቃ ጉባኤ

የሕንድና የአፍሪቃ የምጣኔ ሐብት የጋራ ትብብር ሁለተኛ ስብሰባና ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተጀመረ። የአካባቢያዊ ምጣኔ ሐብታዊ ማሕበራትና ድርጅቶች ባለሥልጣናት ዛሬ ከተወያዩ በሕዋላ ነገ-የሁለቱ ወገኖች መልዕክተኞች በሚንስትሮች ደረጃ ይሰበሰባሉ።

default

በመጪዉ ሳምንት ደግሞ የአፍሪቃ እና የሕንድ መሪዎች ጉባኤ ይደረጋል።የሕንድ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ቪሽኑ ፕራካሽ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደገለጡት ስብሰባና ጉባኤዉ ከምጣኔ ሐብቱ ግንኙነት ባለፍ የአፍሪቃና የሕንድን ሁለንተናዊ ጥንታዉ ግንኙነት ለማጠናከር ይበጃል።

«የአርባ-አምስት ቢሊዮን ዶላር አመታዊ የንግድ ልዉዉጥ አለን።ሕንድ አፍሪቃ ዉስጥ ከሐምሳ ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ወርታለች።ከዚሕ ይበልጥ በጠም ጠቃሚዉ ነገር በሕንድና በአፍሪቃ መካከል ከፍተኛ መፈላለግና መፈቃቀድ መኖሩ ነዉ።»

የሁለቱን ወገኖች የመጀመሪያ ስብሰባና ጉባኤን ያስተናገደችዉ ሕንድ ነበረች።ካሁኑ ስብሰባና ጉባኤ ጎን ለጎን የባለሙያዎችና የነጋዴዎች ዉይይት ይደረጋል። የንግድ ትርዒድም ይከፈታል።

መሳይ መኮንን
ነጋሸ መሐመድ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic