የሐምቡርጉ ምርጫ ውጤትና አንድምታው | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሐምቡርጉ ምርጫ ውጤትና አንድምታው

በያዝነው በጎሮጎሮሳውያኑ 2011 ዓ.ም በ 7 የጀርመን ፌደራል ክፍለ ግዛቶች ከሚጠበቁት ምርጫዎች አንዱ ባለፈው ዕሁድ በሁለተኛዋ የጀርመን ትልቅ ከተማ በሀሐምቡርግ ተካሂዷል ።

default

ተመራጩ ኦላፍ ሹልትስ

በዚህ ወሳኝ ምርጫም የመሐል ግራ አቋም የሚያራምደው የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር SPD በሰፊ ልዩነት አሸንፏል ። ለ 10 ዓመታት ሀምቡርግን ሲመራ የቆየው የክርስቲያን ዲሞክራቶች ህብረት በጀርመንኛው ምህፃር CDU ታላቅ ሽንፈት ተከናንቦ ቦታውን ለ SPD ለቆ ተሰናብቷል ። የሐምቡርጉ ምርጫ ውጤትና አንድምታው የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ። በትልቅነት ከጀርመን ከተሞች ሁለተኛዋ ሐምቡርግ ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ከተሞች ጋር ስትነፃፀር ደግሞ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ። ይህች ከተማ የ 1.8 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ ስትሆን የአገር ጎብኚዎች መስህብም ናት ። በዚህች የወደብ ከተማ ባለፈው ዕሁድ የተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ ከተማይቱን ለ10 ዓመታት ያስተዳደሩት ክርስቲያን ዲሞክራቶች አሰናብቶ በምትካቸው ሶሻል ዲሞክራቶችን ወደ ሥልጣን አምጥቷል ። ድሉ ለ አሸናፊዎቹ ለሶሻል ዲሞክራቶች በዓይነቱ የተለየ ተብሏል ። ስለ ሐምቡርጉ ምርጫ ውጤትና አንድምታው እንዲሁም በጎርጎሮሳውያኑ 2011 ዓም በሌሎች የጀርመን ፌደራል ክፍለ ግዛቶች የሚካሄዱት ምርጫዎች በወደፊቱ የፖለቲካ አቅጣጫ ላይ ስለሚኖራቸው ወሳኝ ሚና እዚህ ጀርመን የተማሩትንና የሚሰሩትን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋን አነጋግሬያለሁ ። ዶክተር ለማ በእሑዱ ምርጫ SPD የተቀዳጀው ድል ታሪካዊ ሊባል የበቃበትን ምክንያት በማብራራት ይጀምራሉ ። ሂሩት መለሰ አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች