የሊብያ መሪ የኢጣልያ ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 10.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሊብያ መሪ የኢጣልያ ጉብኝት

የሊብያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ ዛሬ በኢጣልያ ታሪካዊ የተባለውን ይፋ ጉብኝት ጀመሩ።

default

እእአ ከ1969 ወዲህ ሊብያን የሚመሩት ጋዳፊ የቀድሞዋን የሀገራቸውን ቅኝ ገዢ ኢጣልያን ሲጎበኙ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። የኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቭዮ ቤርሉስኮኒ እና ሌሎች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሮማ ቺያምፒኖ አየር ማረፊያ በመገኘት ለጋዳፊ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የሊብያው መሪ ሶስት ቀናት በሚቆየው ጉብኝታቸው ወቅት ከኢጣልያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች፡ በአከራካሪው ህገ ወጥ አፍሪቃውያን ስደተኞች ጉዳይ ላይ ጭምር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። እንደሚታወሰው፡ የኢጣልያ ጠቅላይ ሚንስትር ባለፈው ዓመት ሊብያን በመጎብኘት በዚህ ረገድ አንድ ታሪካዊ ውል ከተፈራረሙ ወዲህ የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት እየተሻሻለ መጥቶዋል።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ/አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic