የሊቢያ ጉዳይ ጉባኤ በለንደን እና ድብደባዉ | ዓለም | DW | 29.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሊቢያ ጉዳይ ጉባኤ በለንደን እና ድብደባዉ

የጉባኤዉ አስተናጋጆች እንዳሉት በጉባኤዉ ላይ የአርባ ሐገራት ተወካዮች፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ተጠሪዎች ይካፈላሉ።

default

ክሊንተንና ካምሩን

የተጣማሪዎቹ ሐገራት ጦር በሊቢያ ላይ የሚያደርገዉን የአዉሮፕላንና የሚሳዬል ድብደባ እንደቀጠለ ነዉ።የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊና የተቃዋሚዎቸዉ ታማኞች የሚያደርጉት ዉጊያም አላባራም።ለንደን ዉስጥ ደግሞ ሥለ ሊቢያ የወደፊት ሁኔታ የሚነጋገር አለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል።የጉባኤዉ አስተናጋጆች እንዳሉት በጉባኤዉ ላይ የአርባ ሐገራት ተወካዮች፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ተጠሪዎች ይካፈላሉ።የአፍሪቃ ሕብረት ግን በጉባኤዉ ላይ እንዲካፈል የቀረበለትን ጥያቄ አልተቀበለዉም።ሥለ ጉባኤዉ አለማና ሒደት የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ