የህክምና ተዓምር ፤ በሸረሪት ድር | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 19.01.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የህክምና ተዓምር ፤ በሸረሪት ድር

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ በሥነ ቅመማ አንዳንድ ሙከራዎችን ያከናወኑ ዘንድ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና ባህል ድርጅት ባልደረቦች በሆኑ አዘጋጂዎች ተጠይቀዋል።

default

ፕላስቲክን የሚተካ፣ ለቀዶ ጥገና ህክምና የሚበጅ ድር የሚያበረክቱት ሸረሪቶች፤ በስዕሉ ላይ የምናያትን Nephila Inaurata Madagascar በመባል የታወቀችውን ይመስላሉ።

የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሥነ ቅመማ (Chemistry)መታሰቢያ ዘመን መንስዔ በማድረግ፣ ተማሪዎች በውሃ ላይ 4 ሳይንሳዊ ምርመራዎችን እንዲያካሂዱ ይፈለጋል ። መርኀ-ግብሩ ፣ ፓሪስ ውስጥ በይፋ የሚታወጀው ኀሙስ ጥር 19 ቀን 2003 ዓ ም ነው። የዓለም አቀፉ ንፁህና ተግባራዊ የሥነ-ቅመማ ማኅበር ረዳት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፋቢዬን ማየርስ እንዳሉት ፣ በዚሁ መርኀ-ግብር፣ 10,000 ት/ቤቶች ይሳተፋሉ የሚል ተስፋ አላቸው። ምርምሩ ከሚያተኩርባቸው መካከል፣ በውሃ ውስጥ የአሲድ መኖር-አለመኖር ፣ እንዲሁም ማጣራት ዋንኞቹ ናቸው። በቦርሳዎች የታሸጉ የመለስተኛ የሥነ ቅመማ መመራማሪያ መሣሪያዎች፤ ለአንዳንድ የታዳጊ አገሮች ት/ቤቶች ፣ በእርዳታ መልክ ይላካሉ። የተማሪዎቹ የምርምር ተግባር ከተጠናቀቀ በኋላም፣ ውጤቱ፣ በዓለም አቀፉ የሥነ-ቅመማ መታሰቢያ ዘመን ድረ-ገጽ ላይ ይገለጣል። ጤናይስጥልኝ እንደምን ሰነበታችሁ? በየዘርፉ የሚከናወን ሳይንሳዊ ምርምር፣ ብዙውን ጊዜ ያልተጠበቀም የተጠበቀም ጠቃሚ ውጤት ይመዘገብበታል።

በመሆኑም የሥነ ህይወት ምርምር ውጤት ለከፍተኛ ሥነ ቴክኒክም ሆነ ለረቂቅ የቀዶ ጥገና ህክምና ዐቢይ ተስፋ እንደሚያስጨብጥ የሚያጠራጥር አይደለም ።

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ