ዛሬም እየተደሰቱ-ያዝናሉ፥ እየሳቁ ያነባሉ-ማዲባ | ዜና | DW | 03.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዜና

ዛሬም እየተደሰቱ-ያዝናሉ፥ እየሳቁ ያነባሉ-ማዲባ

የነጭ-ጥቁር ቅይጥ ስብዕና፥ የነፍጥ-ሰላማዊ ትግል አርበኛ

default

ማንዴላ

ለጥቁሩ፥ ለፍትሕ እኩልነት ተሟጋቾች ጥንት፥ ድሮም-ዘንድሮም ለፍትሕ ተሟጋች የሕግ-ሰዉ፥ ለእኩልነት ተከራካሪ-ፖለቲከኛ፤ ለነፃነት ተፋላሚ አርበኛ፥ ሐገር ሕዝብ መሪ-አስተዳዳሪ ናቸዉ።ሌሎች ግን እንደ ዘመኑ ሒደት ብዙ ናቸዉ።ጥንት-እንደ ብዙ ጥቁር ብጤዎቻቸዉ ለአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎች ኋላ ቀር፣ ከእንስሳ የበለጡ-ከሰዉ ያነሱ መገዛት የነበረባቸዉ ፍጡር ነበሩ።ባሪያ።በመሐሉ ለፕሪቶሪያ፣ ለለንደን ዋሽንግተን መሪዎች ኮሚንስት፤ አሸባሪ፤ ታደኑ። ወንጀለኛ ሆነዉ ዘብጥያ ወረዱ።ኋላ የዲሞክራሲ ጠበቃ፤ የሰላማዊ ትግል ቀንዲል፣ በሳል ሐገር መሪ ሆኑ።አሁን የአለም እንቁ ናቸዉ።ዘጠና አመት ሊደፍኑ ሁለትሳምንት ቀራቸዉ።ኔልሰን ሮሊሕላሕላ ማንዴላ።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ልደታቸዉን አስታከን ከዘንቀ-ምግባር ማንነታቸዉ ጭላፊዉን እንቃኛለን አብራችሁን ቆዩ።