ዓ/አቀፍ የወባ መከላከያ ቀን በኢትዮጵያ | ጤና እና አካባቢ | DW | 26.04.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ዓ/አቀፍ የወባ መከላከያ ቀን በኢትዮጵያ

በወባ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር ባለፉት ተከታታይ ዓመታት እየቀነሰ መምጣቱትን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ ዛሬ ታስቦ የዋለዉን የዓለም የፀረ-ወባ ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣዉ ዘገባ እንዳስታወቀዉ

In a photo made Friday, Oct. 30, 2009 a mother holds her baby as she receives a new malaria vaccine as part of a trial at the Walter Reed Project Research Center in Kombewa in Western Kenya.A new vaccine being tested here is giving the medical community hope that for the first time it will soon be able to reduce by half the number of African children killed by the mosquito-borne disease every year. (ddp images/AP Photo/Karel Prinsloo).

የወባ መከላከያ ክትባት

መንግሥታትና አለም አቀፍ ድርጅቶች የወባ በሽታን ለመካለል የሚያወጡት ገንዘብ ባለፉት አስር ዓመታት ብዙ ጨምሯል።የዓለም ጤና ድርጅት የበላይ ማርጋሬት ቻን ትናንት እንዳስታወቁት ባለፉት ዓመታት ወባን ለመከለክልና በሽተኞችን ለማከም ተጨማሪ ገንዘብ በመዉጣቱና ልዩ ትኩረት በመሠጠቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሞት ተርፈዋል።ይሁንና ሐላፊዋ አክለዉ እንዳሉት ወባ አሁንም ከዓለም በርካታ ሕዝብ ከሚገድሉ አምስት በሽታዎች አንዱ ነዉ።

Autor Kletr Portfolio ansehen Bildnummer 34389879 Land Tschechische Republik

Anopheles Mücke

በዚሕም ሰበብ የዘንድሮዉ የፀረ-ወባ ቀን አብይ መርሕ በጣሙን የአፍሪቃ ሕፃናትን የሚፈጀዉን በሽታ ለመከላከል የሚደረገዉ ጥረት እንዲጠናከር የሚጠይቅ ነዉ።በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚንስቴር የወባ መከላከያ ዘርፍ አስተባባሪ ወይዘሪት ሕይወት ሰለሞን እንዳስታወቁት የፀረ-ወባ ዕለት ኢትዮጵያ ዉስጥም ተከብሮ ነዉ የዋለዉ።
የወባ በሽታ መቀነሱ ቢነገርም ባለፈዉ የጎሮጎሮሳዉያኑ አመት ብቻ ከስድስት መቶ ሐምሳ ሺሕ በላይ ሕዝብ በትንሽ ወጪ በሚገዛዉ መድሐኒት እጦት በወባ በሽታ ሞቷል።ከከሟቾቹ ከአምስት መቶ ሥልሳ ሺሕ የሚበልጡት ጨቅላ ሕፃናት ነበሩ።ከሟቾቹ ከዘጠና ከመቶ የሚበልጡት ደግሞ አፍሪቃዉያን ነበሩ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic