ዉይይት፤ የታሳሪዎች የ ″አይደገምም″ ፋይዳና እዉነታዉ | ኢትዮጵያ | DW | 01.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ዉይይት፤ የታሳሪዎች የ "አይደገምም" ፋይዳና እዉነታዉ

የኢትጵያ መንግሥት ባለፈዉ መስከረም ማብቅያ በደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣብያዎች ይዟቸዉ ከነበሩ ከ 12,500 በላይ ሠዎች መካከል 10 ሺ ያህሉን ከአንድ ሳምንት በፊት መልቀቁን አስታዉቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 36:34

የተሃድሶዉና የአይደገምም ፋይዳ

በሃገሪቱ በነበሩት ኹከቶች ዉስጥ ተሳትፈዋል የተባሉት እነዚህ ዜጎች የተለቀቁት በነበሩበት የማሰልጠኛ ጣቢያ መንግሥት ተሃድሶ ያለዉን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ መሆኑም ተነግሯል። መንግሥት እንደሚለዉ እነዚህ ሰዎች የተያዙት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሃገሪቱን ሠላምና መረጋጋት በማወክ የመንግሥትና የግል ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረዉ ነዉ። ሆኖም ይህንን የመንግሥት መግለጫ ገለልተኛ ወገኖች አይቀበሉትም። እስረኞቹ በመቆያ ጣቢያ በነበሩበት ወቅት የተለያየ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ረገጣ እንደተፈፀመባቸዉ ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን እስረኞቹ የተሰጣቸዉን ትምህርት ተከታትለዉ ሁለተኛ አይደገምም የሚል ቃል ገብተዉ መለቀቃቸዉን መንግሥት በሚቆጣጠረዉ መገናኛ ዘዴዎች አስታዉቋል። ሰዎቹ መያዛቸዉ አግባብ ነበረ ወይ? አያያዛቸዉን ምን ይመስል ነበር? ጉዳት በደል ደርሶባቸዉ ከነበረስ ተጠያቂዉ ማነዉ? በዚህ ዉይይታችን የእስሩ እና የተሀድሶውን ፋይዳ እንዳስሳለን። በዉይይቱ እንዲሳተፉልን የጋበዝናቸዉ፤ መንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲየታ  አቶ ዛዲግ አብራሃ፤ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍስሀ ተክሌ፤ የድረ- ገፅ ፀኃፊና በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳይ ተሳታፊ አቶ አሉላ ሰለሞን፤ እንዲሁም፤ ከዞን ዘጠኝ አምደ መረብ ፀሀፊዎች አንዱ የሆኑት አቶ ዘላለም ክብረት ናቸዉ። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች