ወጣቱ በኦሎምፒክስ ሰሞን | ባህል | DW | 10.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ወጣቱ በኦሎምፒክስ ሰሞን

ሎንዶን ከተማ ውስጥ የሚከናወነው 30ኛው የኦሎምፒክስ ጨዋታዎች ውድድር የኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሳበ እየተነገረ ነው። ያነጋገርናቸው ወጣቶች እንደገለፁልን ከሆነ ከኦሎምፒክስ ውድድሩ በፊት በወጣቱ ዘንድ የመነጋገሪያ አርዕስት ሆነው የቆዩት ወቅታዊ ጉዳዮች አሁን በኦሎምፒክስ ውድድሩ ክንውኖች ተቀይረዋል።

ሎንዶን ከተማ ውስጥ የሚከናወነው 30ኛው የኦሎምፒክስ ጨዋታዎች ውድድር የኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ትኩረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሳበ እየተነገረ ነው። ያነጋገርናቸው ወጣቶች እንደገለፁልን ከሆነ ከኦሎምፒክስ ውድድሩ በፊት በወጣቱ ዘንድ የመነጋገሪያ አርዕስት ሆነው የቆዩት ወቅታዊ ጉዳዮች አሁን በኦሎምፒክስ ውድድሩ ክንውኖች ተቀይረዋል። ወጣቶቹ ቀልባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ስለሳበው የኦሎምፒክስ ጨዋታዎች ውድድር፤ በተለይ ስለ ኢትዮጵያውያን ውጤት የተሰማቸውን ደስታ እና ቅሬታ ይገልፁልናል። አብራችሁን ቆዩ።

በመዝናኛ ቦታዎች፣ በስራ ገበታ፣ እቤት ውስጥ አለያም ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሁሉ የሰሞኑ የኅብረተሰቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፤ 30ኛው የኦሎምፒክስ ጨዋታዎች ውድድር። በተለይ ደግሞ አብዛኛው ወጣቱ ክፍል ቀልቡ በዚሁ የኦሎምፒክስ ጨዋታዋች ውድድር እንደተሳበ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልፀውልናል። የ22 ዓመቷ ወጣት ሊዲያ ተሾመ ተማሪ ናት። ውድድሩን ከመጀመሪያው አንስቶ እየተከታተለችው እንደሆነ ትገልፃለች።

ጥሩነሽ ዲባባ በ10000ሜ የወርቅ ባለድል

ጥሩነሽ ዲባባ በ10000ሜ የወርቅ ባለድል

የ21 ዓመቱ ወጣት ናኦል ገበየሁ ደግሞ በአዳማ ዩኒቨርሲቲ 4ኛ ዓመት የሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነው። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሲሳተፉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም የኦሎምፒክስ ውድድር በተቻለው መጠን ለመከታተል ይሞክራል። እስካሁን ዝግጅቱ፣ መርሀ-ግብሩ፣ ውድድሩ አስደስቶኛል ይላል። ይሁንና ግን በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል የመደሰቱን ያህል ቅር የተሰኘባቸው ነገሮችም አልታጡም። ወጣት ናኦል፥

ከስራ ሰአት ውጪ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ኢትዮጵያውያን የሚያከናውኑትን ውድድሮች በአጠቃላይ ትከታተላለች። በሄደችበት ቦታ ሁሉ የወጣቱን ቀልብ የገዛው የኦሎምፒክስ ውድድሩ እንደሆነም ገልፃልናለች። ወጣት ማህሌት ተስፋዬ ትባላለች።

ቲኪ ገላና በማራቶን የወርቅ ባለድል

ቲኪ ገላና በማራቶን የወርቅ ባለድል

30ኛው የኦሎምፒክስ ጨዋታዎች ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የአትሌቲክሱ ፍክክር ይመስጠዋል ወጣት አቤል ተስፋዬን። ከውድድሩ የሚገኘው ማንኛው ሀገራዊ ድል ደግሞ ፅናት እና አሸናፊነትን ያስተምረኛል ይላል።

«ወጣቱ በኦሎምፒክስ ሰሞን» በሚል ርዕስ ያጠናቀርንላችሁ የወጣቶች ዓለም መሰናዶ በዚህ ይጠናቀቃል። ቀሪ ውድድሮች ላይ አትሌቶቻችን ድል እንዲቀናቸው እየተመኘን በዚሁ እንሰናበት፤ ለዝግጅቱ ማንተጋፍቶ ት ስለሺ ነኝ፤ ጤናይስጥልኝ!

ማንተጋፍቶ ት ስለሺ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 10.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/15nHN
 • ቀን 10.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink http://p.dw.com/p/15nHN